በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሚድ-ተርም ምርጫ ምንድነው?


የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤትን ለመቆጣጠር በዕጩ እንደራሴዎች መካከል የሚካሄደው የምረጡኝ ዘመቻ ተጠናክሮ ሰንብቷል።

የሁለቱም ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወዳዳሪ ዕጩዎችም እስከ መጨረሻዋ ደቂቃ እየታገሉ ይገኛሉ።

በሕዝብ አስተያየቶችና በፖለቲካ ሙያተኞች ግምት በዘድሮው 2010 የአማካይ ዘመን ምርጫ ወይም ሚድ ተርም ኤሌክሽን የመጨረሻ ቀናት ውድድር ሬፐብሊካን ተፎካካሪዎች በብዙው ሣይቀናቸው እንደማይቀር ይወራል። የዚህ ምክንያት ደግሞ ከአገሪቱ ወቅታዊ የኤኮኖሚ ሁኔታ ጋር ይያያዛል።

ለመሆኑ ሚድ-ተርም ወይም የአጋማሽ ዘመን ምርጫ ምን ማለት ነው? ሁኔታውን እንደ ኢትዮጵያ ካሉ አገሮች ጋር ማያያዝስ ይቻል ይሆን? ባለሙያ አነጋግረናል። ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረ-ማርያም ይባላሉ። የህግ ጠበቃና በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ መምህር ናቸው። ያወያያቸው ያዲሷበበ መነሻ ጥያቄም ይኸው ነው። ለዝርዝሩ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡XS
SM
MD
LG