በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን አቶ ጌታቸው ረዳን ማገዱን አስታወቀ


መቐለ ከተማ
መቐለ ከተማ
በዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን አቶ ጌታቸው ረዳን ማገዱን አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:29 0:00

በሁለት ቡድኖች ተከፍሎ እየተወዛገበ ከሚገኘው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አመራር ውስጥ፣ ላለፉት ሰባት ቀናት በመቐለ የሰማዕታት ሐወልት አዳራሽ ሲያካሒድ የቆየውን ጉባኤ ዛሬ ሰኞ ያጠናቀቀው በዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የሚመራው ቡድን፣ አቶ ጌታቸው ረዳን ከፓርቲው አባልነት ማገዱን፣ከፓርቲው ምክትል ሊቀ መንበርነትም ማንሳቱን አስታውቋል።

በጉባኤው ያልተሳተፉ ሌሎች አመራሮችንም ከፓርቲ አባልነት ማገዱን ጠቁሟል።

ጉባኤው፣ ዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤልን የህወሓት ሊቀ መንበር አድርጎ መርጧል፡፡ የጉባኤው ቃል አቀባይ የነበሩት አቶ ዐማኑኤል አሰፋ ደግሞ፣ አቶ ጌታቸው ረዳን በመተካት የፓርቲው ምክትል ሊቀ መንበር ኾነው ተመርጠዋል፡፡

የጉባኤው ዝግጅት፥ “የፓርቲውን ደንብ እና አሠራር የጣሰ ነው፤” ሲሉ መካሔዱን ሲቃወሙ የቆዩት እነ አቶ ጌታቸው፣ “ተቃዋሚ የተባሉ አመራሮችን ለማስወገድ ያለመ” እንደኾነም ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድም፣ “ሕጋዊ ሒደቱን አላሟላም” በሚል ለጉባኤው ዕውቅና እንደማይሰጠውና ውሳኔዎቹም ተቀባይነት እንደማይኖራቸው ቀደም ሲል አስታውቋል፡፡

በሌላ በኩል፣ በፓርቲው ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ሌላው የህወሓት ቡድን፣ “ህወሓትን ማዳን” በሚል የጠራውን ስብሰባ፣ ትላንት እሑድ፣ በመቐለ ከተማ በማካሔድ ማምሻውን ባወጣው ባለዐሥር ነጥቦች መግለጫ፣ በእነ ዶ/ር. ደብረ ጽዮን ቡድን የተደረገው ጉባኤ “ሕገ ወጥ ነው፤ ውሳኔዎቹም ተቀባይነት የላቸውም፤” ብሏል፡፡

አቶ ጌታቸው ረዳ በመድረኩ ላይ ባሰሙት ንግግር፣ “ኢ-ሕጋዊ” ባሉት ጉባኤ ተደናግረው የተሳተፉ ያሏቸው የህወሓት አባላት፣ “ወደ ቀልባቸው በመመለስ ከሕዝባቸው ጎን እንዲሰለፉ” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የፓርቲውን አመራሮችና ሕገ ወጥ ባሉት ጉባኤ ተደናግረው የተሳተፉ ያሏቸውን የህወሓት ካድሬዎች ጭምር በማሳተፍ ፓርቲያቸውን ለማዳን እንደሚሠሩም ገልጸዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG