በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመቐለ ወጣቶች "ሰርጌን" የተሰኘ ነፃ መጽሄት አቋቋሙ


የሰርጌ መፅሄት መስራቾች
የሰርጌ መፅሄት መስራቾች

መቐለ ከተማ ውስጥ ከአሁን በፊት "ፊደል ሰራዊት" በሚል ተደራጅተው የንባብ ክበብና የሥነ ጽሑፍ ምሽት ስያካሂዱ የነበሩ 12 ወጣቶች በአሁኑ ሰዓት ያሳተሙት የግል መፅሔት ባለፈው ሣምንት በይፋ ተመርቆ ለንባብ በቅቷል።

“ሰርጌን” ማለት በአማርኛ “ሰርገኛ ጤፍ” ማለት ሲሆን ትርጉሙም የተለያየ ሃሳቦችን የሚያስተናግድ መድረክን መፍጠር ማለት እንደሆነ መስራቾቹ ገልፀዋል።

የመጽሔቱ ዋና አዘጋጅ ደስታ ገብረመድህን "አማራጭ ማቅረብ ተቃውሞ አይደለም፤መንግሥትና ህዝብ ይህንን እውነታ ሊረዱልን ይገባል" ብሏል።

ከመፅሔት አዘጋጆቹ አንዱ የሆነው ሶፋንያስ ዳርጌ “የትግራይ ህዝብ ነፃ መዲያን በማግኘት በኩል የሚገባውን ያህል ያልተገለገለ ህዝብ ነው” ይላል።

ሰርጌ መፅሄት
ሰርጌ መፅሄት

በመጀመርያው የሰርጌን የህትመት ውጤት በተለይም ብዙ ወጣት መጽሔቱን አግኝቶ ማንበቡንና ገንቢ አስተያየት መስጠቱን ይህም ለወደፊቱ ጥሩ ግብአት መሆኑን ሃይለአብ ሃይለሥላሴ ተናግሯል።

ትግራይ ክልል ውስጥ ከአሁን በፊት ይታተሙ የነበሩ መፅሔቶችና ጋዜጦች ረዥም ርቀት ሳይጓዙ ይቋረጡ እንደነበሩ ይታወቃል፤ ይህም የተለያዩ ውስጣዊና ውጫዊ ምክንያቶች እንደሚጠቀሱ አዘጋጆቹ ይገልፃሉ።

ትግራይ ውስጥ በአሁኑ ሰዓት "ውራይና" እና "ፍኖተ ሰሜን" የተሰኙ መፅሔቶች ታትመው ስርጭት ላይ ይገኛሉ።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የመቐለ ወጣቶች "ሰርጌን" የተሰኘ ነፃ መጽሄት አቋቋሙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:12 0:00

XS
SM
MD
LG