መቀሌ —
መቀሌ ከተማ ውስጥ “ምድረ ገነት” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ “ሕገወጥ” ተብለው ከስምንት ዓመታት በፊት መኖሪያ ቤቶቻቸው የፈረሱባቸው ነዋሪዎች ለአቤቱታዎቻቸው መልስ የሚሰጣቸው አካል ማጣታቸውን በመግለፅ እያማረሩ ናቸው።
ለአቤቱታቸው ምላሽ ሳይሰጥ አካባቢው በዶዘር እየተጠረገ መሆኑ እንዳስከፋቸውም ነዋሪዎቹ ገልፀዋል።
አካባቢው በዶዘር እየተጠረገ ያለው “የፈረሱ ቤቶቻቸውን አሻራ ለማጥፋት” ነው ብለዋል አቤት ባዮቹ የመቀሌ ነዋሪዎች።
“ቤቶቹ የፈረሱት ሕጋዊ የይዞታ ሰነድ ስለሌላቸው ነው” ያለው የመቀሌ ሐድነት ክፍለ-ከተማ በበኩሉ ቦታው እየተጠረገ ያለው በልማት ምክንያት ለሚፈናቀሉ የቤት ባለቤቶች ለመምራት መሆኑን አመልክቷል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ