በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማሮና በጉጂ ግጭት መንግሥት ኃላፊነት ሊወስድ ይገባል ተባለ


ችግሩ የተከሰተው በድንበር ማካለልና ማስፋፋት እንቅስቃሴ ምክንያት መሆኑን በመጥቀስ ለዚህ ችግር መንግሥት ኃላፊነት ወስዶ በአፋጣኝ ሁኔታውን ወደነበረበት እንዲመልስ ፓርቲው በመግለጫው ጠይቋል።

በደቡብ ክልል የአማሮና በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን መካከል በሁለት ተጎራባች ወረዳዎች ለሁለት ቀናት ማለትም እሁድ ሐምሌ 16 እና ዕረቡ ሐምሌ 19 በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ለጠፋው የ13 ሰዎች ሕይወት፣ ለቆሰለው ሰውና ለወደመው ንብረት መንግሥት ሐላፊነት ወስዶ፤ የግጭቱ መንስኤ የሆኑ የድንበር ማስፋፋት እንቅስቃሴዎችን በአስቸኳይ እንዲያስቆምና ግጭቱን በዘላቅነት ሊያስወግድ የሚያስችል እርምጃ በአፋጣኝ እንዲወሰድ የመድረክ አባል ፓርቲ የሆነው የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ አሳሰበ።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

በአማሮና በጉጂ ግጭት መንግሥት ኃላፊነት ሊወስድ ይገባል ተባለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:22 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG