በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጉጂና አማሮ ግጭት የ13 ሕይወት ጠፋ


Guji
Guji

•የአካባቢው ነዋሪዎች ከዚህ በፊት እንዲህ ያለ ግጭት አጋጥሞን አያውቅም ብለዋል። በደቡብ ክልል አማሮ ሕዝብ (ኮሬ ጎሳ)ና በኦሮሚያ ክልል በጉጂ ዞን አጎራባች ወረዳ ነዋሪዎች መካከል የመጀመሪያው ግጭት የተጀመረው እሁድ ሐምሌ 16/2009 ዓ.ም መሆኑን ተናግረዋል።

በጉጂና አማሮ ግጭት የ13 ሕይወት ጠፋ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:44 0:00

ግጭቱ ሐምሌ 19/2009 ዓ.ም እንደገና አገርሽቶ በሁለቱም በኩል የ13 ሰው ሕይወት መጥፋቱን የሁለቱ ክልል መንግሥታት አረጋገጡ። በተጨማሪም ቤቶች ተቃጥለዋል፣ ከ400 በላይ አባወራዎች ተፈናቅለዋል በርካታ ሰዎችም ቆስለዋል ተብሏል።

የአካባቢው ነዋሪዎ ሁለቱ ሕዝቦች ለረጅም ዘመናት ተጋብተውና ተዋልደው የኖሩ ከዚህ ቀደም ግጭት አጋጥሞ እንደማያውቅ ገልፀው "ለዚህ ከፍተኛ አደጋ የዳረገው ጉዳይ ግራ አጋብቶናል" ብለዋል።

አሁን በቦታው መከላከያ ሠራዊት ቢገባም ውጥረቱ እንዳለና መንገድ ዝግ እንደሆነም ይናገራሉ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG