በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በመኪና አደጋ ህይወቱ ያለፈው ኬንያዊው የማራቶን ክብረ ወሰን ባለቤት ኬልቪን ኪፕቱም

በመኪና አደጋ ህይወቱ ያለፈው ኬንያዊው የማራቶን ክብረ ወሰን ባለቤት ኬልቪን ኪፕቱም
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:04 0:00

በመኪና አደጋ ህይወቱ ያለፈው ኬንያዊው የማራቶን ክብረ ወሰን ባለቤት ኬልቪን ኪፕቱም

በረጅም ርቀት ኮከብ ሯጭ እንደሚሆን ተስፋ የተጣለበት የዓለም የማራቶን ሪከርድ ባለቤት ኬልቪን ኪፕቱም፣ ከአሠልጣኙ ጋራ በደረሰበት የመኪና አደጋ ትላንት እሁድ የካቲት 3/2016 ዓ.ም ህይወቱ አልፏል።

ባለፈው ዓመት ቺካጎ ላይ በተካሄደው ውድድር የዓለም ክብረወሰን የሰበረው የ24 ዓመቱ ኪፕቱም በማራቶን ፣ ከረጅም ዓመታት በኋላ በረጅም ርቀት ሩጫ አስደናቂ ውጤት ያመጣሉ ተብለው ትልቅ ተስፋ ከተጣለባቸው አትሌቶች አንዱ ነው። በነሐሴ ወር በፓሪስ በሚካሄደው ማራቶን ወርቅ ያመጣሉ ተብለው ከሚጠበቁ ተፎካካሪዎችም አንዱ ነበር።

ኬንያዊው ኪፕቱም እና ሩዋንዳዊው አሠልጣኙ ጌርቪስ ኻኪዚማና በመኪና አደጋው ህይወታቸው ያለፈው ከምሽቱ አምስት ሰዓት አካባቢ መሆኑን፣ ኬንያዊቷ አትሌት ሚልካ ቼሞስ ለአሶስዬትድ ፕሬስ ገልጻለች።

ቼሞስ ከአደጋው በኋላ የተወሰዱበት ሆስፒታል የነበረች ሲሆን፣ አስክሬናቸውን ማየቷንም ተናግራለች።

ቼሞስ ከሚተናነቃት እምባ ጋር እየታገለች "ኬልቪንን ማጣት ምን ማለት እንደሆነ መግለፅ አልችልም" ብላለች።

የመኪና አደጋው የደረሰው በምዕራብ ኬንያ፣ ኤልዶሬት እና ካፕታጋት ከተሞች መካከል ላይ ባለው መንገድ ላይ መሆኑን ያስረዳችው ቼሞስ ስፍራው ከባህር ወለል ባለው ከፍታ እና ለኬንያውያን እና ከመላው ዓለም ለሚመጡ የረጅም ርቀት ሯጮች ለሥልጠና የተመቸ መሆኑን ገልጻለች። ኪፕቱም ተወልዶ ያደገው በዚሁ አካባቢ ነው።

ቼሞስ የአትሌቱን የሕልፈት ዜና ከሰማች በኃላ ከሌሎች አትሌቶች እና የኪፕቱም ቤተሰቦች ጋር ወደ ሆስፒታል መሄዷን ገልፃ፣ የኪፕቱምን አባት ጨምሮ ቤተሰቦቹ አስክሬኑን አይተው ማንነቱን ማረጋገጣቸውንም ተናግራለች።

የካፕታጋት ከተማ የፖሊስ ኃላፊ ዴኒስ ሙጋ፣ መኪናውን ያሽከረክር የነበረው እራሱ ኪፕቱም መሆኑን እና ሌላ አደጋ የደረሰበት መኪና አለመኖሩን ገልጸዋል።

በመኪና አደጋ ህይወቱ ያለፈው ኬንያዊው የማራቶን ክብረ ወሰን ባለቤት ኬልቪን ኪፕቱም ያሽከረክራት የነበረችው መኪና የመኪና አደጋው ከደረሰበት፣ ካፕታጋት ከተሞች መካከል በምዕራብ ኬንያ፣ ኤልዶሬት እእአ የካቲት 12/2024
በመኪና አደጋ ህይወቱ ያለፈው ኬንያዊው የማራቶን ክብረ ወሰን ባለቤት ኬልቪን ኪፕቱም ያሽከረክራት የነበረችው መኪና የመኪና አደጋው ከደረሰበት፣ ካፕታጋት ከተሞች መካከል በምዕራብ ኬንያ፣ ኤልዶሬት እእአ የካቲት 12/2024

አደጋው እንደተከሰተ ወዲያው አካባቢው ላይ እንደደረሰ የገለጸው የኪፕቱም ጓደኛ በበኩሉ ኪፕቱም ከመኪናው ውጪ ተወርውሮ ወድቆ እንዳየው ተናግሯል። ምናልባትም መኪናው በከፍተኛ ፍጥነት ከመንገድ ሳይወጣ እንደማይቀር እና ከመንከባለሉ በፊት ከዛፍ ጋር መጋጨቱን ገልጿል። በመኪናው ውስጥ የነበረች ሌላ ሦስተኛ ሴት ከባድ ጉዳት ደርሶባት ወደ ሆስፒታል ተወስዳለችም ብሏል። አደጋው በደረሰበት ስፍራ የተነሱ ፎቶዎች፣ ብርማ ቀለም ያለው መኪና ጣሪያው ተጨራምቶ እና አንደኛው በሩ ተገንጥሎ ወድቆ ያሳያሉ።

የኬንያ ሩጫ ፌዴሬሽን የኪፕቱምን እና ኻኪዚማናን ሞት ዜና ባስታወቀበት ወቅት የተሰማውን ከፍተኛ ሃዘን ገልጿል።

ኪፕቱም ማራቶንን ከሁለት ሰዓት ከአንድ ደቂቃ በታች መሮጥ የቻለ የመጀመሪያው አትሌት ሲሆን፣ በጥቅምት ወር ቺካጎ ላይ ተካሂዶ በነበረው ውድድር 2:00.35 በመግባት፣ በሌላኛው ኬንያዊ ኢሉይድ ኪፕቾጌ ተይዞ የነበረውን ሪከርድ ሰብሯል። በፓሪሱ ውድድር ኪፕቱም እና ኪፕቾጌ ወርቅ ለማግኘት ይፋለማሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር።

የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሴባስቲያን ኮይ፣ ትዊተር ተብሎ ይጠራ በነበረው፣ ኤክስ ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ሀዘናቸውን የገለፁ የመጀመሪያው ሰው ሲሆኑ፣ "ኬልቪን ኪፕቱም እና አሰልጣኙ ጌርቫስ ኻኪዚማና በደረሰባቸው አደጋ መሞታቸውን ስንሰማ በጣም አዝነናል። በዓለም አትሌቲክስ ስም፣ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለጓደኞቻቸው፣ ለስፖርት ባልደረቦቻቸው እና ለመላው የኬንያ ህዝብ መፅናናትን እንመኛለን" ብለዋል።

በመኪና አደጋ ህይወቱ ያለፈው ኬንያዊው የማራቶን ክብረ ወሰን ባለቤት ኬልቪን ኪፕቱም ያሽከረክራት የነበረችው መኪና የመኪና አደጋው ከደረሰበት፣ ካፕታጋት ከተሞች መካከል በምዕራብ ኬንያ፣ ኤልዶሬት እእአ የካቲት 12/2024
በመኪና አደጋ ህይወቱ ያለፈው ኬንያዊው የማራቶን ክብረ ወሰን ባለቤት ኬልቪን ኪፕቱም ያሽከረክራት የነበረችው መኪና የመኪና አደጋው ከደረሰበት፣ ካፕታጋት ከተሞች መካከል በምዕራብ ኬንያ፣ ኤልዶሬት እእአ የካቲት 12/2024

በ800 ሜትር ሁለት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮን የሆነው ኬንያዊው ዴቪድ ሩዲሻ በበኩሉ፣ የኪፕቱም ሞት "ትልቅ ጉዳት ነው" ሲል ኤክስ ላይ ፅፏል።

እ.አ.አ በ2022 ቫሌንሺያ ላይ ተካሂዶ በነበረው የማራቶን ውድድር ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ ውጤት ማምጣት የጀመረው ኪፕቱም በአመቱ በለንደን እና ቺካጎ የተደረጉ ውድድሮችን አሸንፏል።

ኪፕቱም ገና ወጣት እና አትሌቲክሱን አዲስ የተቀላቀለ ቢሆንም፣ በመኪና አደጋዎች ህይወታቸውን ካጡ የኬንያ ሯጮች መካከል አንዱ ሆኗል። የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች የብር ሜዳሊያ አሸናፊ የነበረው ዴቪድ ሌሊ እ.አ.አ በ2010 በደረሰበት የመኪና አደጋ ህይወቱ ሲያልፍ፣ የማራቶን ተወዳዳሪው ፍራንሲስ ኪፕላጋት፣ እ.አ.አ በ2018 በደረሰ የመኪና አድጋ ከሞቱት አምስት ሰዎች መካከል አንዱ ነው። እ.አ.አ በ2015፣ በ400 ሜትር መሰናክል የዓለም ሻምፒዮና ውድድር ወርቅ ያሸነፈው ኒኮላስ ቤትም፣ እ.አ.አ በ2018 በመኪና አደጋ ህይወቱ አልፏል።

በመካከለኛ ርቀት ሩጫ የሚታወቀው ሩዲሻ፣ የቀድሞው የ10 ሺህ ሜትር ተወዳዳሪው ሞሰስ ታኑኢ እና፣ የኦሎምፒክ ብር ሜዳሊያ ተሸላሚ ፖውል ቴርጋትም ከከባድ የመኪና አደጋዎች ተርፈዋል።

የኦሎምፒክ ማራቶን ሻምፒዮን የነበረው ሳሙኤል ዋንጂሩ፣ እ.አ.አ በ2011 በ24 ዓመቱ፣ መኖሪያ ቤቱ ከነበረበት ፎቅ ላይ ወድቆ መሞቱ ይታወሳል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG