ዋሺንግተን ዲሲ —
ሆቴል ሩዋንዳ በተባለው ፊልም ታሪካቸው የተወሳላቸው ሰው በሃገሪቱ ፍርድ ቤት በአሸባሪነት፣ በግድያ በመመሳጠርና የታጠቀ አማፂ ቡድን በማቋቋም ወንጀል ተከሰሱ።
ፖል ሩሴሴባጊና ከሁለት ዓመታት በፊት ያልታጠቁ ሰላማዊ የሩዋንዳ ዜጎች ላይ ጥቃት እንዲፈፀም አሲረዋል ሲል አቃቤ ህግ ከሷቸዋል።
እርሳቸው አሥራ ሦስቱንም የተመሰረቱባቸውን ክሶች አስተባብለው ቃላቸውን ሲሰጡ የተመሰረተባቸውን ክስ መሰረተ ቢስ ነው ብለዋል።
በእሥር ላይ ያሉት ፖል ሩሴሳቤጊና በህመም ምክንያት እንዲለቀቁ የጠየቁ ሲሆን ፍርድ ቤቱ የፊታችን ሃሙስ አቤቱታቸውን ሊያደምጥ ቀጠሮ ሰጥቷል።
በሩዋንዳ የዘር ፍጅት ወቅት የአንድ ሆቴል ሥራ አስኪያጅ የነበሩት ፖል ሩሴሳቤጊና አያሌ ቱትሲዎችን ደብቀው ከገዳዮች ጥቃት ያስመለጡ ጀግናነት ታሪካቸው በሆቴል ሩዋንዳ ፊልም ተወስቶላቸዋል። አንድ ሺህ የሚሆኑ ሰዎችን ህይወት እንዳተረፉ ነው የሚነገርላቸው።