በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ሆቴል ሩዋንዳ" በተባለው ፊልም በጀግንነት የተገለጹት ግለሰብ በእሥር ላይ ናቸው


ፎቶ ፋይል ፓል ሩዘሳባጊናን
ፎቶ ፋይል ፓል ሩዘሳባጊናን

"ሆቴል ሩዋንዳ" በተባለው ፊልም በጀግንነት የተገለጹት ሩዋንዳዊ፣ አማጽያንን ረድተዋል በሚል ክስ፣ ለፍርድ ይቀርባሉ ሲሉ፣ የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንት ካጋሜ በብሄርዊ ቴሌቪዥን ቀርበው ሲናገሩ፣ ፓል ሩዘሳባጊናን እንዴት ወደ ሩዋንዳ እንደተወሰዱ አልገለጹም። ተከሳሹ ከአንድ ሳምንት በላይ ለሆነ ጊዜ በእስር እንደሚገኙ ታውቋል።

እአአ በ1994 ሩዋንዳ ውስጥ ፍጅት ይፈፀም በነበረበት ወቅት፣ ያስተዳድሩት በነበረው ሆቴል ውስጥ በመደበቅ፣ ከ1,200 በላይ የሚሆኑ ስዎችን፣ ከግድያ ለማትረፍ ችለዋል በሚል ሲሞገሱ ኖረዋል።

አሁን ግን ሩዋንዳ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ አማጽያንን ረድተዋል በሚል ተከሰዋል። ቤተሰባቸው ላነጋግራቸው አልቻልኩም። ለጠበቃም ተደራሽነት የላቸውም ሲል አማሯል።

XS
SM
MD
LG