በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በማሊው ራዲሰን ሆቴል የቀሩ ታጋቾች እንደሌሉ የሃገሪቱ ባለስልጣኖች አስታወቁ


በማሊው ባማኮ በሚገኘው ራዲሰን ሆቴል የደረሰ የሽብር ጥቃት
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:16 0:00

በማሊው ባማኮ በሚገኘው ራዲሰን ሆቴል የደረሰ የሽብር ጥቃት

እስላማዊ ጥቅሶችን የሚያሰሙ አማጽያን ዛሬ በማሊ መዲና ላይ የሚገኝ በምዕራባውያን የሚዘወተር ትልቅ ሆቴልን ተቆጣጥረው 170 የሚሆኑ ሰዎችን አግተው ነብር። አሁን ግን በሆቴሉ የቀሩ ታጋቾች እንደሌሉ የማሊ ባለስልጣኖች ገልጸዋል።

የማሊ ልዩ ሃይሎች ባማኮ በሚገኘው ራዲሰን ብሉ በተባለው ሆቴል የታገቱትን ስዎች ለማስለቀቅ የሆቴሉ ደረጃዎችን አንድ በአንድ እያሰሱ ይንቀሳቀሱ እንደነበር የጸጥታ ምንጮች ጠቁመዋል።

ከታገቱት 170 ስዎች ሰማንያ እንደተለቀቁ ተገልጾ ነበር። መጀመርያ ላይ ሆቴሉን የያዙት ቢያንስ 4 ታጣቂዎች ሲሆኑ ቁርአን ለመድገም የቻሉትን ሰዎች እንደለቀቁ ተገልጿል። ታጣቂዎቹ ወደ ሆቴሉ የሄዱት የዲፕሎማቶች ታርጋ ባላቸው መኪኖች እንደሆነ ተዘግቧል።

አፍሪካ ኮማንድ የተባለው የዩናትድ ስቴትስ (United States) ወታደራዊ እዝ ከእገታ ነጻ እንዲወጡ የተደረጉት ታጋቾች ስድስት አሜሪካውያን እንደሚገኙባቸው ገልጿል። የአሜሪካ ወታደራዊ ሰራተኞች ከሆቴሉ ውጭ ሆነው እየረዱ መሆናቸውን አፍሪቃ ኮማንድ ጠቁሟል።

ሮይተርስ የዜና አገልግሎት በገለጸው መሰረት ዐል-ማውራቢቱን የተባለ በሰሜን ማሊ የሚገኝ ከዐል-ቓዒዳ ጋር የተሳሰረ ቡድን ለጥቃቱ ሃላፊነት ወስዷል። ይሁንና ይህን ለመረጋገጥ የሚቻልበት መንገድ የለም።

ማሊ ለብዙ አመታት ከዐል-ቓዒዳ ጋር የተሳሰረ ቡድንን ስትፋለም ቆይታለች። በያዝነው አመት ቀደም ሲል በደቡባዊ ማሊ በሚገኝ ሆቴል ላይ ለተከፈተው ጥቃትም ከዐል-ቓዒዳ

ጋር የተሳሰሩ ቡድኖች ሃላፊነት ወስደው ነበር።

ፈረንሳይ በታጋቾች ጉዳይ ልዩ ሙያ ያለው ወታደራዊ ቡድን እየላከች ነው። ማሊ የፈረንሳይ ቅኝ ግዛት እንደነበረች የሚታወቅ ነው።

Katarina Hoije የተባለችው ዘጋብያችን ግን እስካሁን ባለው ጊዜ ያየሁት ወታደራዊ ሃይል የለም ብላለች።

“ፈረንሳውያኑ ወታደሮች በአብዛኛው በሰሜን ማሊ ጸረ አሸባሪ እንቅስቃሴ በማካሄድ ላይ ነው ያሉት። በመዲናይቱ ብዙም አይታዩም” ብላለች ዘጋቢዋ።

በአሁኑ ወቅት ማሌዣን በመጎብኘት ላይ ያለቱ የ United States ፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ የማሊውን ሁኔታ እየተከታተሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ማሊ ያለው የአሜሪካ ኤምባሲ ያወጣው መግለጫ “ኤምባሲው በራዲሰን ሆቴል ውስጥ ተኩስ እንዳለ ተገንዝቧል። ሁሉም የአሜሪካ ዜጎችና የኤምባሲው ሰራተኞች ካሉባት እንዳይንቀሳቀሱ ኤምባሲው ያሳስባል ይላል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰላም ጠባቂ ሀይሎች በሀገሪቱ ያሉ ቢሆንም ማሊ ውስጥ እንዲህ አይነት ጥቃት መከፈቱ በሰሜንና በማዕከላዊ ማሊ የሚንቀሳቀሱት እስላማዊ አማጽያን አደጋ የመደቀናቸው ጉዳይ መቀጠሉን ያሳያል።

የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘጋቢ ካትሪና ሆይጄ (Katarina Hoije) ከባማኮ የላከቸውን ዘገባ አዳነች ፍሰሀየ ታቀርበዋለች። የድምጽ ፋይሉን በመጫን ያዳምጡ።

በማሊው ራዲሰን ሆቴል የቀሩ ታጋቾች እንደሌሉ የሃገሪቱ ባለስልጣኖች አስታወቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:59 0:00

XS
SM
MD
LG