በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዲሱ የማሌዥያ ንጉሥ


አዲሱ የማሌዥያ ንጉሥ
አዲሱ የማሌዥያ ንጉሥ

አዲሱ የማሌዥያ ንጉሥ ዛሬ በተደረገው የንግሥና ስነ ሥርዓት በትረ ሥልጣኑን በኦፊሴል ተረክበዋል።

አዲሱ የማሌዥያ ንጉሥ ዛሬ በተደረገው የንግሥና ስነ ሥርዓት በትረ ሥልጣኑን በኦፊሴል ተረክበዋል።

ሱልጣን አንዱላህ ሱልጣን አሕመድ ሻህ ኩዋላ ላምፑር በሚገኘው ብሄራዊ ቤት መንግሥት 16ኛው የሀገሪቱ ንጉሥ ሆነው ተሰይመዋል። የንግሥናው ስነ ሥርዓት በቴሌቪዥን ታይቷል።

አዲሱ የማሌዥያ ንጉሥ
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:14 0:00

ጠቅላይ ሚኒስትር መሐቲር ሞሐመድ በስነ ሥርዓቱ ከተገኙት ባለሥልጣናት መካከል ነበሩ። የ59 ዓመት ዕድሜው ሱልጣን አብዱላህ ሱልጣን ሙሐማድን ተክተው ነው የተሰየሙት።

ሱልጣን ሙሐማድ ሥልጣን ላይ የቆዩት ለሁለት ዓመታት ላልሞላ ጊዜ ቢሆንም እአአ ጥር 6 ቀን ሳይታሰብ ከሥልጣን ተሰናበቱ። ከሥልጣን የተሰናበቱት ለሳምንታት ያህል የህክምና ፈቃድ ከወሰዱ በኋላ ነው። ከዚያም አንዲት በውበትዋ የምትደነቅ ወጣት ሩስያዊት አግብተዋል የሚል ጭምጭምታ ሲሰማ ቆይቷል።

ሙስሊምች የሚበዙባት ማሌዥያ እአአ በ1957 ዓም ከብሪታንያ ቅኝ አገዛዝ ነፃ ከውጣችበት ጊዜ አንስቶ ንጉሥዋ ከሥልጣን ሲሰናበት ሱልጣን ሙሐመድ የመጀመሪያው ናቸው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG