No media source currently available
አዲሱ የማሌዥያ ንጉሥ ዛሬ በተደረገው የንግሥና ስነ ሥርዓት በትረ ሥልጣኑን በኦፊሴል ተረክበዋል። ሱልጣን አንዱላህ ሱልጣን አሕመድ ሻህ ኩዋላ ላምፑር በሚገኘው ብሄራዊ ቤት መንግሥት 16ኛው የሀገሪቱ ንጉሥ ሆነው ተሰይመዋል። የንግሥናው ስነ ሥርዓት በቴሌቪዥን ታይቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር መሐቲር ሞሐመድ በስነ ሥርዓቱ ከተገኙት ባለሥልጣናት መካከል ነበሩ። የ59 ዓመት ዕድሜው ሱልጣን አብዱላህ ሱልጣን ሙሐማድን ተክተው ነው የተሰየሙት።
አስተያየቶችን ይዩ
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ