በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢማኑኤል ማክሮን በዩናይትድ ስቴትስ


የፈረንሣይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በዩናይትድ ስቴትስ የሦስት ቀናት ሙሉ መንግሥታዊ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ዋሺንግተን ዲ.ሲ. ይገባሉ።

የፈረንሣይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በዩናይትድ ስቴትስ የሦስት ቀናት ሙሉ መንግሥታዊ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ዋሺንግተን ዲ.ሲ. ይገባሉ።

ማክሮን አሜሪካ ውስጥ በሚቆዩባቸው ቀናት የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች ከእሥላማዊ መንግሥት ቡድን ሽንፈት በኋላም ቢሆን ሶሪያ ውስጥ እንዲሰነባብቱ ፕሬዚዳንት ትረምፕን ለማሳመንና የአውሮፓ ኅብረትን ከአሉሚነምና ከብረት ታሪፋቸው ውጭ እንዲያደርጉም ለመማለድ እንደሚጥሩ ተገልጿል።

“ከጦርነቱ በኋላም አዲሲቱን ሶሪያን መገንባት ይኖርብናል፤ ለዚህ ነው የዩናይትድ ስቴትስ ሚና እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው የምለው” ብለዋል ፕሬዚዳንት ማክሮን ለጉዟቸው ከመነሣታቸው በፊት ፋክስ ኒውስ ለሚባለው የዜና አውታር ፓሪስ ላይ በሰጡት መግለጫ።

“ለሰላምና ለዘርፈብዙነት ዩናይትድ ስቴትስ መተኪያ የሌላት ሃገር ነች” ብለዋል ማክሮን።

“ከሶሪያ የምንወጣ ከሆነ ሜዳውን ለቅቀን የምንወጣው ለኢራንና ለአሳድ እንደሚሆን በቀጥታ መናገር እፈልጋለሁ” ያሉት ሚስተር ማክሮን ሩሲያና ቱርክም ሊጫወቱት የሚችሉት ገንቢ ሚና ሊኖር እንደሚችል አመልክተዋል።

የኢራንን የኒኩሌር መርኃግብር ውል አስመልክቶም ሲናገሩ ምንም እንኳ ፍፁም ነው ባይባልም ለጊዜው ውሉ ባለበት እንዲቀጥል እንደሚፈልጉም ፕሬዚዳንት ማክሮን ተናግረዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG