ምዕራብ ለንደን ውስጥ በቅርቡ “ግሬንፌል” የሚባለው 24 ፎቆች ያሉት የመኖሪያ ሕንፃ በእሣት ጋይቶ የ79 ሰዎች ሕይወት ከጠፋ በኋላ ተመሳሳይ አደጋዎችን ለመከላከል በብሄራዊ ደረጃ ምርመራ ተጀምሯል።
በዚሁ መሠረት ከትላንት በስቲያ ቅዳሜና ዕሁድ በመላ ብሪታንያ በተካሄዱ ምርመራዎች በትንሹ ስልሣ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች የደኅንነት ምርመራውን ማለፍ ሳይችሉ መቅረታችውን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። ምርመራው አንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
የማኀበረሠብና የአካባቢው መንግሥታዊ መሥሪያ ቤት ብሄራዊ የእሳት መከላከያ ደኀንነት ምርመራውን በሚያካሂድበት ወቅት ስጋት ባሳደሩ ሌሎች በርካታ ሕንፃዎች ላይ የሚኖሩ ሰዎችን ለደኀንነታቸው ሲባል እንዲያስወጡ ታዘዋል።
እርምጃውን ተከትሎ ባሳለፍነው ዓርብ 8መቶ አባወራዎች ባጭር ጊዜ ውስጥ በተሰጠ ትዕዛዝ ይኖሩበት ከነበረው አፓርተማ አንዲወጡ ተደርጓል። ከእነርሡም መካከል ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል።
ሰሎሞን ክፍሌ አንድ ኢትዮጵያዊ የአስቸኳይ ጊዚው መመሪያ ሰለባ አነጋግሯል።
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ