አዲስ አበባ —
ዕሁድ፣ መስከረም 9/2008 ዓ.ም. አገልግሎት መስጠት የጀመረው የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ከተማይቱን ለማዘመንና የመጓጓዣ ችግርን ለማቃለል የሚያግዝ መሆኑን አስተያየት የሰጡ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በግንዛቤ እጥረትና በቂ ማቋረጫዎች ባለመኖራቸው ምክንያት አደጋዎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ የትራንስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ወርቅነህ ገበየሁ አሳስበዋል።
ከአገልግሎቱ መጀመር ጋርም የሚኒስትሮች ምክር ቤት የባቡር አገልግሎት ደህንነት አዋጅ አውጥቷል።
የትራንስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ወርቅነህ ገበየሁ "አገልግሎት ጋር በተያያዘ አንድም ሰው ከባቡር እንዲሞት አንፈልግም" ብለዋል።
ለዝርዝሩ ከታች የተያያዘውን የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ የድምፅ ማጫወቻውን ተጭነው ያዳምጡ።