ዋሺንግተን ዲሲ —
በሊቢያ በሕገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች ቤዛ ገንዘብ እንዲከፍሉ ታግተው የሚገኙ ወደ ሁለት መቶ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያንና ሶማሊያዊ ፍልሠተኞችና ስደተኞችን ለመስለቀቅ የዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት /IOM/ እየጣረ መሆኑን አስታወቀ።
ስደተኞችን በማፈን ሕግ በማይከበርባቸው የማቆያ ጣቢያዎች የሚያሳዩ የቪዲዮ ምስሎች በማህበራዊ ድረ ገፅ ወይንም በፌስ ቡክ ባሳለፍነው ሳምንት በሰፊው ሲታዩ ነበር፡፡
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ