በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሊቢያ ኢትዮጲያውያን ስደተኞች በጸረ ጋዳፊው ዓመጽ ውስጥ ተጠምደው የጥቃት ሰለባ መሆናቸውን አስታወቁ


በጸረ መንግሥት ተቃውሞ እየተናጠች ከምትገኘው ከሊቢያ ብዙ ሺህ የውጭ ሀገር ዜጎች በአውሮፕላን ፥ በመርከብም ይሁን በዕግር ብቻ ባገኙት መንገድ ዕግሬ አውጪኙን ተያይዘውታል

በጸረ መንግሥት ተቃውሞ እየተናጠች ከምትገኘው ከሊቢያ ብዙ ሺህ የውጭ ሀገር ዜጎች በአውሮፕላን ፥ በመርከብም ይሁን በዕግር ብቻ ባገኙት መንገድ ዕግሬ አውጪኙን ተያይዘውታል።

በሊቢያ ያሉ ኢትዮጲያውን ስደተኞች እየተፋፋመ ባለው ህዝባዊ ዓመጽና በየጸጥታ ኃይሉ በያዘው ርምጃ መካከል ተጠምደዋል።

የሀገሪቱ መሪ ሞአማር ጋዳፊ በተቃውሞ በተነሳባቸው ህዝብ ላይ ባዕዳን ቅጥረኛ ወታደሮችን አስገብተው ማስደብደብ ይዘዋል እየተባለ ባለበት በዚህ ወቅት ኢትዮጲያውያኑ ስደተኞች በትሪፖሊና በቤንጋዚ ብቅ ስንል በጸረ መንግሥት ተቃዋሚዎች ጥቃት ዒላማ እየተደረግን ነው በማለት ያሉበትን አስፈሪ ሁኔታ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG