“የሄዝቦላህ አባላት የሚጠቀሙባቸውን ኤሊክትሮኒክ የመልዕክት መቀባበያዎች (ፔጀሮች) ያፈነዳች እስራኤል ነች” ሲሉ ሄዝቦላህ እና የሊባኖስ መንግሥት ወንጅለዋታል። ትላንት ማክሰኞ በደረሱት ፍንዳታዎች ሁለት ህጻናትን ጨምሮ ቢያንስ አስራ ሁለት ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች ወደ 2800 የሚሆኑ ቆስለዋል፡፡ ሄዝቦላ የጋዛን የሃማስ ታጣቂዎች በመደገፍ ከእስራኤል ጋር መዋጋታችንን እንቀጥላለን ሲል ዛሬ ሐሙስ ተናግሯል፡፡ አክሎም “እስራኤል የሚደርስባትን ከባድ ቅጣት ትጠብቅ” በማለት ዝቷል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ብሊንክን ዛሬ ካይሮ ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል “ዩናይትድ ስቴትስ ስለፍንዳታው የምታውቀው ነገር አልነበረም፡፡ የለችበትምም” ብለዋል፡፡ አያይዘውም የአካባቢው ውጥረት መባባሱ እንደሚያሳስባቸው ጠቁመዋል፡፡
ብሊንክን ከግብጽ አቻቸው ባድር አብደላቲ ጋር ሆነው ባደረጉት ጋዜጣዊ ጉባኤ ሁሉም ወገኖች ግጭቱን ሊያባብስ ከሚችል አድራጎት ሊቆጠቡ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡ የግብጹ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አብደላቲ በበኩላቸው ፍንዳታውን እና የሊባኖስን ሉዓላዊነት የሚጥስ ማናቸውንም ድርጊት ሲሉ የገለጹትን አውግዘዋል፡፡ “አጠቃላይ ጦርነት አፋፍ ላይ ነን” ማለታቸው ተጠቅሷል፡፡
እስራኤል ጋዛ ላይ በሀማስ ታጣቂዎች በሀማስ ታጣቂዎች ላይ የምታካሂደው ጦርነት ሰሜናዊ ግዛቷን ከሄዝቦላ የሮኬት ጥቃት መከላከልን እንዲጨምር አድርጋ እንደምታስፋፋው ካስታወቀች ሰዓታት በኋላ ስለደረሰው ፍንዳታ አስተያየት አልሰጠችም፡፡
የኢኤክትሮኒክ መልዕክት መቀባበያ ፔጀሮቹ የፈነዱት ለሄዝቦላ ከመላካቸው በፊት ጥቂት መጠን ያለው ፈንጂ ተጨምሮባቸው ነው የሚል ጥርጣሬ አለ፡፡ የሄዝቦላ መሪ “ለእስራኤል ስለላ እና ክትትል ያጋልጠናል” በሚል ስጋት የቡድኑ አባላት በተንቀሳቃሽ ስልክ እንዳይጠቀሙ ካዘዘ በኋላ አባላቱ በአመዛኙ የሚጠቀሙት በጥሪ ማቀባበያዎቹ ፔጀሮች መሆኑ ተመልክቷል፡፡
መድረክ / ፎረም