በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሊባኖስ ተንቀሳቃሽ የመልዕክት መቀበያዎች ፈንድተው ዘጠኝ ሰዎች ሞቱ፣ ብዙዎች ተጎዱ


ከቤሩት ከተማ ዳርቻና በሌሎችም የሌባኖስ ክፍሎች የሚገኙ በደርዘኖች የሚቆጠሩ ሰዎች የተንቀሳቃሽ መልዕክት መቀበያ መሳሪውያዎች (ፔጀሮች) ፈንድተው ዘጠኝ ሰዎች ሲሞቱ፣ በመቶ የሚቆጠሩ ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው የሊባኖስ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን እና የደህንነት ኃላፊዎች አስታወቁ፡፡

አንድ የሊባኖስ ከፍተኛ የወታደራዊና ደህነንት ባለስልጣን እና ሌላ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ግለሰብ፤ ከሁኔታው አሳሳቢነት አንጻር ማንነታቸው እንዳይገልጽ ጠይቀው አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን ሁለቱም በሂዝቦላ አባላት ጥቅም ላይ የሚውሉ ተንቀሳቃሽ የመልዕክት መቀበያ መሳሪያዎች ፈንድተዋል ያሉ ሲሆን፤ በተጨማሪም ጥቃቱ በእስራኤል የተፈጸመ ነው ብለው እንደሚያምኑ ሁለተኛው ምንጭ ተናግረዋል፡፡

የሀገሪቱ ብሔራዊ የዜና ጣቢያ በደቡባዊ ቤሩት ከተማ ዳርቻ እና በሌሎች ቦታዎች የደረሱት ጉዳቶች “በእጅ የሚያዙት ተንቀሳቃሽ የመልዕክት መቀበያዎች የፈነዱት በላቀ ቴክኖሎጂ አማካይነት ኢላማ ስለተደረጉ ነው” ያለ ሲሆን በደርዘኖች የሚቆጠሩ ሰዎች መጎዳታቸውን ዘግበዋል፡፡

የሄዝቦላ ባላስልጣናት በተለያዩ የሊባኖስ የከተማ ክፍሎች ያሉ አባላቱን ጨምሮ 150 ሰዎች መጎዳታቸውን አስታውቀዋል፡፡ ለመገናኛ ብዙሃን መረጃ ለመስጠት ፍቃድ የሌላቸው አንድ ማንነታቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የሄዝቦላ ሃላፊ “ፍንዳታዎቹ እነዚህን የመልዕክት መቀበያ መሳሪያዎች ዒላማ ያደረጉ ጥቃት ውጤት ናቸው” ብለዋል፡፡

አሶሽየትድ ፕሬስ በጉዳዩ ላይ የእስራኤል መከላከያን ምላሽ ለማግኘት ያደርገው ጥረት እንዳለተሳካለት ዘግቧል፡፡

የሄዝቦላ መሪ ሀሰን ናስረላህ ከዚህ ቀደም የቡድኑ ዓባላት በእስራኤል ደህነንቶች ያሉበት ሊታወቅ እንደሚችል በመግለጽ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን እንዳይዙ አስጠንቅቀው ነበር፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG