ሀዋሳ —
በደቡብ ክልል በኮንሶና በአሌ ልዩ ወረዳ በመሬት ይዞታ ምክንያት ተቀስቅሶ የቆየው ግጭት እንደቀጠለ ሲሆን በዚሁ ሰበብ በዘመን መለወጫ ቀናትም ከሁለቱም በኩል አራት ሰዎች መገደላቸውና ቤቶች መቃጠላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
የመንግሥት ባለሥልጣናትን ጨምሮ ለግጭቱ ሰበብ ሆነዋል የተባሉ የፖለቲካ ሰዎች በህግ እንዲጠየቁ እየተደረገ ነው ሲል የክልሉ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ገልጿል።
በሁለቱ አዋሳኝ ቀበሌዎች ውስጥ የሚገኘው የደን መሬት “ይገባኛል” በሚል በተነሳው ግጭት የብዙ ሰው ህይወት የጠፋ ሲሆን ከሃያ ሺህ በላይ ሰው መፈናቀሉም ተነግሯል።
ኮንሶ ዞንና አሌ ልዩ ወረዳ ከለውጡ በፊት «የሰገን አከባቢ ህዝቦች ዞን» ተብሎ ከአማሮ፣ ከቡርጂና ከደራሼ ጋር በአንድነት የነበሩ ሲሆን ኮንሶ፤ ዞን ሆኖ ብቻውን ከተደራጀ በኋላ አሌም እንደተቀሩት በልዩ ወረዳነት የተደራጀ መዋቅር ነው።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።