ሀዋሳ —
በደቡብ ክልል በኮንሶ ዞን እና አከባቢው በተፈጠረ ግጭት ለተፈናቀሉ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረግ መጀመሩን የክልሉ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ገለጠ።
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ጋንታ ጋምአ የተፈናቀሉ ዜጎችን በተመለከተ እንደተባለው 90ሺህ እንደማይደርስ ገልጸው፣ ትክክለኛው ቁጥር የተለያዩ አካላትን አካቶ በተደራጀ ኮሚቴ እየተጣራ መሆኑን ለቪኦኤ አስታውቀዋል።
ቪኦኤ ግጭቱ ከተቀሰቀባቸው እና ብዙ ዜጎች ተፈናቀሉ ከተባለው ከኮንሶ ዞን ኮልሜና ቀበሌ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች አንፃራዊ ያሉት ሰላም መኖሩን ገልፀው በቂ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዳልደረሰላቸው ተናግረዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡