ሀዋሳ —
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ በድጋሚ በተቀሰቀሰ ግጭት ሰባት ሲቪሎች መገደላቸው እና ቁጥራቸው በውል ያልተገለጹ ቤቶች መቃጠላቸውን የወረዳው አስተዳደር አስታወቀ።
ግጭቱ እንደገና የተቀሰቀሰው የራሳቸውን አስተዳደራዊ መዋቅር ለመፍጠር የሚፈልጉ እና ደራሼ ወረዳ የተወጣጡ አካላት የትርምስ ሴራ ነው ሲሉ አስተዳዳሪው ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ከስሰዋል።
ሁከቱ ከደራሼ ልዩ ወረዳ ጋር አይገናኝም ያሉት የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ አመኑ ቦጋለ ይልቁንስ በሁከት የተነሳ ከሰገን ዙሪያ ወረዳ የተፈናቀሉ ከ25 ሺህ በላይ ዜጎችን ማስጠለላቸውን ተናግረዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።