በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ ክልል ግጭት የተጠረጠሩ መያዛቸው ተገለፀ


በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን፣ አማሮ፣ ዴራሼ፣ ኧሌና ቡርጂ ልዩ ወረዳዎች እና በአካባቢያቸው ተፈጥሮ በነበረው ግጭት በቀጥታና በተዘዋዋሪ እጃቸው አለበት ያላቸውን 137 ተጠጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ።

በደቡብ ክልል ግጭት የተጠረጠሩ መያዛቸው ተገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:58 0:00


በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዲ ዛሬ ለቪኦኤ እንዳስታወቁት በግጭቱ 66 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ሌሎች 39 ሰዎች ቆስለዋል፤ መጠኑ በውል ያልታወቀ አያሌ ቤቶችና ንብረት ወድመዋል።

ከ133 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችንም መፈናቀላቸውንና መልሶ የማቋቋም ሥራ እየተሰራ መሆኑንም ሃላፊ አስታውቀዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG