በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቂሊንጦ ቃጠሎ ተከሳሾች በድጋሚ ለብይን ተቀጠሩ


ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በተቃጠለበት ወቅት
ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በተቃጠለበት ወቅት

በእስር ላይ እያሉ በቂሊንጦ ቃጠሎ በ"ሽብር" የተከሰሱት 38 ተከሳሾች "ይከላከሉ ወይንም በነፃ ይሰናበቱ" የሚለውን ብይን ለማዳመጥ ለትላንት ተይዞላቸው የነበረው ቀጠሮ በሌሉበት እንደተራዘመ ከጠበቆቹ አንዱ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።

ከተከሳሾቹ ጠበቆች መካከል አንዱ አቶ ወንድሙ ኢብሳ ለአሜሪካ ድምፅ ሁኔታውን ሲያስረዱ፤ ፍርድ ቤቱ ለትናንት ቀጥሮ የነበረው ለብይን ቢሆንም ተከሳሾቹ ችሎት ሳይቀርቡ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል ብለዋል። ይህንንም በቅሬታ መልክ ለዳኞች ማስረዳታቸውን ገልፀው ቀጠሮ የተለወጠው ብይኑ ተሠርቶ ባለመጠናቀቁ እንደሆነ መገለፁን ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የቂሊንጦ ቃጠሎ ተከሳሾች በድጋሚ ለብይን ተቀጠሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:06 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG