በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቂሊንጦ ቃጠሎ ተከሳሾች የፍርድ ቤት ውሎ


የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ
የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ

ፍርድ ቤቱ ዐሥራ አንዱን መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ ይሰናበቱ ብሏል። አራቱ በነፍስ መግደል ወንጀል ይከላከሉ ተብሏል። 23 ደግሞ ከነፍስ መግደል ወንጀል በመልሰ ባለው ወንጀል ይከላከሉ ተብሏል። ከጠበቆቹ አንዱ አቶ ወንድሙ ኢብሳ ስለ ዛሬው የችሎት ማብራሪያ ሰጥተውናል።

የቂሊንጦ ማረሚያ ቤትን በማቃጠል ክስ ተመስርቶባቸው ከነበሩት 38 እስረኛ ተከሳሾች መካከል ዐስራ አንዱ መከላከል ሳያስፈለጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱ ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጠ።

አራቱ በነፍስ ግድያ ወንጀል የቀረበባቸውን ክስ እንዲከላለሉ ሲወስን ቀሪዎች ደግሞ ክሳቸው ተሻሽሏል በተሻሻለው ክስ ተከላከሉ ተብለዋል።

በዚህ መዝገብ የተከሰሱ ተከሳሾች ድርጊቱን አልፈፀምንም በአንፃሩ ያልፈፀምነውን ድርጊት እንድናምን ከፍተኛ የማሰቃየት ተግባር ተፈፅሞብናል በሚል ሲከራከሩ እንደነበር ይታወቃል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ)

የቂሊንጦ ቃጠሎ ተከሳሾች የፍርድ ቤት ውሎ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:04 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG