ዋሽንግተን ዲሲ —
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ (John Kerry) በጣም ስለምንተዋወቅና አብረን ችግሮችን የመፍታት ችሎታም አለን በማለት ነዉ ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃምን ጋር ለመነጋገር ቁጭ ያሉት።
ኬሪ በሁሉም በኩል የሚካሄደዉን የአመጽ ቅስቀሳ ማስቆም በጣም አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል። የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃምን ናታንኛሁ አመጹን በመቀስቀስ ፊሊስጤማዉያንን ወንጅለዋል።
ዉጭ ጉዳይ ሚኒስት ኬሪ የፊታችን ቅዳሜ ደግሞ ከፍሊስጤማዉን መሪ መሃሙድ አባስ ጋር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ዜና አቅራቢአችን ፓም ዶኪንስ (Pam Dockins) የላከችዉን ዘገባ ትርጉም ይድምጡ።