በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኬሪ ስለ ሁለት መንግሥታት መፍትኄ


ፎቶ ፋይል/አሶሼትድ ፕሬስ/
ፎቶ ፋይል/አሶሼትድ ፕሬስ/

የተሰናባቹ የኦባማ አስተዳደር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ አብዝተው የሚያሳስቧቸው የእሥራኤል ፍልስጥኤም ግጭት በዘላቂነት የሚቆምበት ጉዳይና የእሥራኤል ጥቅምና ደኅንነትም የሚጠበቅባቸው መላዎች መሆናቸውን እየተናገሩ ነው፡፡

ተሰናባቹ ኬሪ ትናንት ባደረጉት አብይ የተባለ ንግግራቸው ለዚያ የመካከለኛው ምሥራቅ አልቋጭ ያለ የሰላም ችግር መፍትሄ ይሰጣል ያሉትን ራዕያቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለአንድ ሰዓት ያህል ሲናገሩ የአንድ እሥራኤል ፍልስጥኤም መንግሥት ምሥረታ የእሥራኤልን ደኅንነትም ሆነ ጥቅም አያስጠብቅም ብለዋል፡፡ የሁለት መንግሥታት መፍትኄ “እጅግ የከበደ” ባሉት አደጋ ላይ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዋይት ሃውስ ከገቡ በኋላ ለእሥራኤል የሚሰጡት ድጋፍ እንደማይናወጥ አስታውቀዋል፡፡

ለአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መልሳቸውን ፈጥነው የሰጡት የእሥራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ የኬሪ ንግግር ሆን ተብሎ ፍልስጥኤማዊያንን ለመጥቀም የተወጠነጠነ ነው ሲሉ ነቅፈውታል፡፡ የኬሪ ንግግር የተዛባ ነው ብለዋል ኔታንያሁ፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ኬሪ ስለ ሁለት መንግሥታ መፍትኄ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:39 0:00

XS
SM
MD
LG