በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኬሪ በእሥራኤል ጉዳይ የአስተዳደራችውን አቋም ተከላከሉ


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ከፍተኛ አደጋ ላይ ወድቋል ያሉትን የእስራኤልና ፍልስጥኤም የሁለት መንግሥታት ምስረታ መፍትሄ አስመልክተው ዛሬ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ሚኒስትር ኬሪ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪታ ቤት ባደረጉት ንግግር ባለፈው ሳምንት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት በተላለፈው እስራኤል በሰፈር ግንባታዎች ምክንያት በተወገዘችበት ውሳኔ ሀገራቸው የወሰደችውን አቋም ትክክለኛነት አስረድተዋል፡፡

"በተባበሩት መንግሥታት የተሰጠው ድምፅ የሁለት መንግሥታት ምስረታ መፍትሄውን የመጣበቅ ጉዳይ ነበር፡፡ የኛም አቋም እሱ ነው፡፡ እስራኤል እንደ አይሁድ እና ዲሞክራሲያዊ ሀገር የመኖር መብት እንዲጠበቅ ነው" ሲሉም አብራርተዋል፡፡

በፕሬዚዳንት ባራክ ኦባም የሥልጣን ዘመን ማጠናቀቂያ ላይ የተወሰደው ይህ ከእስራኤል መሪዎችና በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ዲሞክራትና ሪፖብሊካን አባላት በኩል ብርቱ ነቀፋ አስከትሏል፡፡

"ዩናይትድ ስቴትስ ከረጅም ጊዜ አጋርዋ ጋር ሳትቆም ቀረታለች" ብለዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ኬሪ በእሥራኤል ጉዳይ የአስተዳደራችውን አቋም ተከላከሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:38 0:00

XS
SM
MD
LG