በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዳዳብን መጠለያ ጣቢያ እንዳይዘጋ የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትዛዝ ሰጠ


ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ መንግሥቱ የዳዳብን መጠለያ ጣቢያ እንዳይዘጋ ከለከለው።

ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ መንግሥቱ የዳዳብን መጠለያ ጣቢያ እንዳይዘጋ ከለከለው። በመጠለያ ጣቢያ፣ ወደ 2መቶ 58ሺሕ የሚጠጉ የሶማልያ ስደተኞች እንደሚገኙበት ይታወቃል። የኬንያ መንግሥት መጠለያ ጣቢያውን እንደሚዘጋ ባለፈው ግንቦት ወር አስታውቆ የነበረ ሲሆን፣ የሰባዓዊ መብት አስከባሪዎች ናቸው አቤቱታውን ያቀረቡት።

የኬንያው ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዳስታወቀው፣ የዓለማችን ትልቁ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ዳዳብ፣ እንደተከፈተ ይቆያል ዜናውን ይፋ ያደረጉትም፣ መጠለያ ጣቢያው እንዲዘጋ መንግሥት ያሳለፈውን ውሳኔ ዛሬ ሐሙስ የሻሩት የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዳኛ ጆን ማቲቮ ናቸው።

“የሶማልያ ስደተኞች ላይ ያነጣጠረው ያ የመንግሥቱ ውሳኔ፣ ከጅምላ ግድያ አይተናነስም። ሕገ ወጥ በደልና አድሎአዊ ነው። ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ፣ ሕገ መንግሥቱን የሚጥስ ነው።”

እንዲዘጋ የተደረገው የስደተኞች ጉዳይ መሥሪያ ቤትም እንዲከፈት፣ ዳኛ ማቲቮ ወስነዋል። የኬንያ መንግሥት፤ ይህን ወደ ወደ 2መቶ 58ሺሕ የሶማልያ ስደተኞችን የሚያስጠልለውን የዳዳብን ጣቢያ ለመዝጋት ውሳኔ ያሳለፈው እአአ ባለፈው 2016 ዓ.ም ግንቦት ወር እንደነበር አይዘነጋም። ውሳኔው ለተጨማሪ ስድስት ወራት እንዲራዘም መደረጉም ይታወቃል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የዳዳብን መጠለያ ጣቢያ እንዳይዘጋ የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትዛዝ ሰጠ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:28 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG