በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ኑሯችንን ተረጋግተን መምራት አልቻልንም" በዳዳብ ስደተኞች ጣቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

በዓለም ትልቁ የሆነው የዳዳብ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሌላ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ እንደሚዘዋወሩ የኬንያ መንግሥት እንደገለፀላቸውና፤ በአሁኑ ወቅት ኑራቸው በእንጥልጥል መቆየቱን ያስረዳሉ።

በዳዳብ ከሚኖሩ 300ሽሕ ስደተኞች በበርካታ ሽዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንም ይገኙባቸዋል። በተለይ ሶማሊያዊያን ስደተኞች ወደሀገራቸው እንዲመለሱ የኬንያ መንግሥት ውሳኔ ቢያሳልፍም፤ ተፈፃሚነቱ ለስድሥት ወራት ተራዝሟል።

ዳዳብ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ በአሁኑ ወቅት ወደ 300ሽሕ የሚጠጉ ስደተኞችን ሲያስጠልል፤ ከእነዚህ መካከል ወደ 12ሽሕ የሚሆኑት ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን የተ.መ.ድ የስደተኞ ኮሚሽን/ዩኤን ኤች ሲ አር/ መዝግቧል።

በዳዳብ በሚገኙ በርካታ ጣቢያዎች ስደተኞች በሸራና በፕላስቲክ ድንኳኖች ከመኖር አንስቶ የንግድ ተቋማትን መስርተው የሚኖሩ በርካታ ስደተኞችም የሚገኙበት ነው፤ በደጋሃሌ ጣቢያ የኢትዮጵያ ምግብ ቤትም አለ።

በ1990ዎቹ ወደ ዳዳብ የተሰደዱ ሶማሊያዉያን ዛሬ የአውቶቡሶች፣ ሱቆችና ሆቴሎች ባለቤትም ለመሆን በቅተዋል።

በዚህ ጣቢያ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን መካከል ለአሜሪካ ድምፅ የሶማሊኛ ዝግጅት ክፍል ሲናገሩ፤ ወደ ካኩማ የስደተኞ መጠለያ ጣቢያ እንደሚዛወሩ ቢነገራቸውም፤ ኑሯቸውን ተረጋግቶ ለመምራት የሚያስችል ሁኔታ አለመፈጠሩን አስረድተዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

"ኑሯችንን ተረጋግተን መምራት አልቻልንም" በዳዳብ ስደተኞች ጣቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:21 0:00

XS
SM
MD
LG