በኬንያ 42 ሴቶችን መግደሉንና አስከሬናቸውንም መቆራረጡን አምኗል የተባለው ግለሰብ ናይሮቢ ከሚገኝ እስር ቤት እንዲያመልጥ ተባብረዋል የተባሉ አምስት ፖሊሶች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
የ33 ዓመቱ ኮሊንስ ጁማኤይሲ እና ሌሎች 12 ኤርትራውያን በመዲናዋ ከሚገኝ የፖሊስ ጣቢያ እስር ቤት ትላንት ማምለጣቸውን ተከትሎ ፖሊስ አሰሳ ጀምሯል።
ፖሊስ “አደገኛ እና ለሰው የማያዝን” ብሎ የገለጸው ግለሰብ ባለፈው ወር በጥርጣሬ የተያዘው የበርካታ ሴቶች አስከሬን በአንድ የቆሻሻ መጣያ ስፍራ ተቆራርጦ መገኘቱን ተከትሎ ነው።
ፖሊስ እንደሚለው ኮሊንስ ጁማኤይሲ የትዳር አጋሩን ጨምሮ 42 ሴቶችን ገድሎ አካላችውን መቆራረጡን አምኗል።
በቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ ሰቆቃ እንደተፈጸመበት ግለሰቡ ለፍርድ ቤት ተናግሯል።
ኮሊንስ ጁማኤይሲ እና በቁጥጥር ሥር የነበሩት 12 ኤርትራውያን ትላንት ከፖሊስ ጣቢያው ያመለጡት ከሽቦ የተሠራዉን ጣሪያ ቆርጠው በመውጣት እንደሆነ የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።
አስራ ሁለቱ ኤርትራውያን ታስረው የነበረው በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ኬንያ ገብተዋል በሚል እንደሆነ ሪፖርቱ አመልክቷል።
መድረክ / ፎረም