በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 
ኬንያ ውስጥ ተቆራርጠው ተጥለው በተገኙት የሰውነት አካላት ጉዳይ የተያዘው ተጠርጣሪ ከእስር አመለጠ

ኬንያ ውስጥ ተቆራርጠው ተጥለው በተገኙት የሰውነት አካላት ጉዳይ የተያዘው ተጠርጣሪ ከእስር አመለጠ


ፎቶ ፋይል፦ ተጠርጣሪው ኮሊንስ ጁማሲ ካሉሻ
ፎቶ ፋይል፦ ተጠርጣሪው ኮሊንስ ጁማሲ ካሉሻ

42 ሴቶችን መግደሉን ያመነው እና ተቆራርጠው በተጣሉት የሰውነት አካላት ጉዳይ ‘እጁ አለበት’ ሲል በቁጥጥር ስር አውሎት የነበረው ተጠርጣሪ ከእስር ማምለጡን የኬንያ ፖሊስ አስታወቀ።

ኮሊንስ ጁማሲ ካሉሻ በወንጀሉ ተጠርጥሮ የተያዘው መርማሪዎች ክስ ከመመስረታቸው አስቀድሞ ወንጀሉን እንዲያጣሩ ፍርድ ቤት ሰባት ተጨማሪ ቀናት ከፈቀደላቸው በኋላ ነው። ሆኖም የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊው እንዳስረዱት፤ ካሉሻ ከሌሎች 12 እስረኞች ጋር በመሆን ዛሬ ማለዳ ላይ የእስር ቤቱን ሽቦ በመቆራረጥ፣ የቅጥር ጊቢውን አጥር ዘሎ አምልጧል። ድንገቱን እየመረመረ መሆኑን ያስታወቀው ፖሊስ ተጠያቂዎች ላይ እርምጃ እወስዳለሁ ብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG