በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬልቪን ኪፕቱም አስከሬን ወደ ትውልድ መንደሩ ተሸኘ

ከአንድ ሳምንት በፊት በመኪና አደጋ ሕይወቱ ያለፈው ኬንያዊው የማራቶን ክብረ ወሰን ባለቤት ኬልቪን ኪፕቱም አስከሬን፣ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ታጅቦ ወደ ትውልድ መንደሩ ተሸኝቷል።

የዓለምን የማራቶን ክብረ ወሰን ከ 2 ሰዓት በታች ለማድረግ ያልም የነበረው ኬልቪን ኪፕቱም፣ ባለፈው ዓመት በአሜሪካ ቺካጎ ከተማ በተደረገ ውድድር 2 ሰዓት ከ 35 ሰከንድ በማጠናቀቅ የዓለምን ክብረ ወሰን ይዟል። ኬልቪን ኪፕቱም በአገሩ ልጅ ኤሊውድ ኪፕቾጊ አንድ ዓመት ቀድም ብሎ ተይዞ የነበረውን የ 2፡01፡09 ሪከርድ አሻሽሉ ነበር ክብረ ወሰኑን የነጠቀው።

የ24 ዓመቱ ኬልቪን ኪፕቱም ከአስለልጣኙ ጋራ በመሆን በስምጥ ሸለቆ መኪናውን በማሽከርከር ላይ ሳለ፣ መኪናው ከቁጥጥሩ ውጪ ሆኖ ከአንድ ዛፍ ጋራ ሲጋጭ የሁለቱም ሕይወት እንዳለፈ የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል። በተደረገው የአስከሬን ምርምራም ጭንቅላቱ በመጎዳቱ ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል ተብሏል።

ኬልቪን ኪፕቱም በመጪው ሚያዚያ ሮተርዳም ላይ በሚደረገው የማራቶን ውድድር ከሁለት ሰዓት በታች ለማጠናቀቅ ተስፋ አድርጎ ነበር። እንዲሁም በፓሪስ ኦሊምፒክ ከአገሩ ልጅ ኤሊውድ ኪፕቾጊ ጋር ከፍተኛ ትንቅንቅ እንደሚያደርጉ በመጠበቅ ላይ ነበር።

የኬልቪን ኪፕቱም አስክሬን 80 ኪ.ሜ. በመጓዝ በእረኝነት ወዳደገባት ቼፕሳሞ መንደር ተጉዞ፣ ነገ ዓርብ የቀብሩ ሥነ ስርዓት እንደሚፈጸም ታውቋል።

ኪፕቱም ባለትዳር እና የሁለት ልጆች አባት ነው።

የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ለቤተሰቦቹ መኖሪያ ቤት እንዲሠራ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG