በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሄይቲ እና ኬንያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጀመሩ


ተጓዦች በፖርት-አው-ፕሪንስ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ በሄይቲ እአአ ቅዳሜ ነሐሴ 5/2023
ተጓዦች በፖርት-አው-ፕሪንስ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ በሄይቲ እአአ ቅዳሜ ነሐሴ 5/2023

ሄይቲ እና ኬንያ ከትናን ረቡዕ ጀምሮ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መጀመራቸውን አስታውቀዋል።

ሁለቱ ሀገራት ይህን ያስታወቁት፣ ኬንያ በተመድ የሚደገፍ የጸጥታ ኃይል በሄይቲ ከወሮበሎች ጋር በመፋለም ላይ ያለውን የፖሊስ ኃይል ለማገዝ ወታደሮቿን ልታሰማራ ትችላለች ተብሎ በሚጠበቅበት ወቅት ነው።

በአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የ ዕራብ ንፍቀ ክበብ ረዳት ጸሃፊ፣ ብራያን ኒኮልስ፣ ለቪኦኤ እንደተናገሩት፣ የተመድ የጸጥታው ም/ቤት ከሀገራት የተውጣጣ ኃይል ወደ ሄይቲ መላክን በተመለከተ በሳምንት ውስጥ ድምጽ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

የሄይቲ መንግስት ካለፈው ጥቅምት ጀምሮ ዓለም አቀፍ እገዛ እንዲደረግለት ሲጠይቅ የቆየ ቢሆንም፣ ኬንያ ባለፈው ሐምሌ ዓለም አቀፍ የጸጥታ ኃይልን ለመምራት ፈቃደኝነቷን እስከምትገልጽ ድረስ ሰሚ አላገኘም ነበር።

የሄይቲ ፖሊስ ኃይል፣ ባለው ውስን አቅርቦት፣ በሀገሪቱ በርካታ ቦታዎችን የተቆጣጠሩትን ወሮበሎች ሲፋለም ቆይቷል።

የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ እና የሄቲው ጠ/ሚ አሪያል ሄንሪ፣ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መጀመራቸውን በማስመልከት በኒው ዮርክ የኬንያ ቆንጽላ ጽ/ቤት ትናንት ሰነድ ፈርመዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG