በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኬኒያ በሄይቲ መድብለ ብሄራዊ ሃይልን ለመምራት ዝግጁ መሆኗን አስታወቀች

የዋና ከተማዋ 80 በመቶ በተደራጁ የውንብድና ቡድኖች እጅ ውስጥ በሚገኝባት ሄቲ ውስጥ ፣ ለገንዘብ ብሎ ሰዎችን ማፈን ፣ በትጥቅ የታጀበ ዝርፊያ ፣ እና የመኪና ንጥቂያን የመሰሉ ከባድ ወንጀሎች ተንሰራፍተዋል ።
የዋና ከተማዋ 80 በመቶ በተደራጁ የውንብድና ቡድኖች እጅ ውስጥ በሚገኝባት ሄቲ ውስጥ ፣ ለገንዘብ ብሎ ሰዎችን ማፈን ፣ በትጥቅ የታጀበ ዝርፊያ ፣ እና የመኪና ንጥቂያን የመሰሉ ከባድ ወንጀሎች ተንሰራፍተዋል ።

ኬንያ ተቀባይነት ካገኘች ፣ግጭት ባየለባት የካሪቢያን ደሴት ሄይቲ ውስጥ ከሀገራት የሚውጣጣ ኃይልን ለመምራት ብሎም 1000 የፖሊስ መኮንኖችን ለማሰማራት ዝግጁ መሆኗን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በትናትናው ዕለት አስታውቀዋል ።

የዋና ከተማዋ 80 በመቶ በተደራጁ የውንብድና ቡድኖች እጅ ውስጥ በሚገኝባት ሄቲ ውስጥ ፣ ለገንዘብ ብሎ ሰዎችን ማፈን ፣ በትጥቅ የታጀበ ዝርፊያ ፣ እና የመኪና ንጥቂያን የመሰሉ ከባድ ወንጀሎች ተንሰራፍተዋል ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እና የሄይቲ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤሪኤል ሄንሪ የሀገሪቱን ፖሊስን ለመደገፍ ዓለም አቀፍ ጣልቃ ገብነት እንዲኖር ለአንድ አመት ያህል ሲጠይቁ ቆይተዋል ። ሆኖም ግን አንድም ሀገር በፍቃደኝነት ወደፊት መምጣት ሳይችል ቆይቷል።

የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አልፍሬድ ሙቱዋ ቅዳሜ አመሻሹን በሰጡት መግለጫ ፣ ኬንያ የሄይቲ ፖሊስን ለማሰልጠን እና ሀገሪቱን ወደ ነበረችበት ለመመለስ የሚያደረግውን ጥረት ለማገዝ ብሎም ቁልፍ ተቋማትን ለመከላከል 1,000 የፖሊስ መኮንኖችን ለማሰማራት ቀርጠኛ መሆኗን ተናግረዋል ።

ስምሪቱ ግን የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት እንዲሁም የሀገር ውስጥ ባለስልጣናት ይሁንታ እንደሚያስፈልገው ሚኒስትሩ አክለዋል።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን አርብ ምሽት ከኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር በስልክ መነጋገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማቲው ሚለር ተናግረዋል።

በምስራቅ አፍሪካ ውስጥ የዴሞክራሲ ተምሳሌት ሆና የምትታየው በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሶማሊያን ጨምሮ በቀጣናዋ የሰላም ማስከበር ስራዎች ላይ ሰትሳተፍ ቆይታለች ።

ስለ ሄይቲው ስምሪት ግን ሌላ ዝርዝር መረጃ ወዲያውኑ አልተገኘም።ዘገባው የኤኤፍፒን ነው

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG