ቁጥጥር የሌለበት የኬንያ የምርጫ ወጪ በዲሞክራሲያዊ ሂደት ላይ ተጽእኖ እንዳያሳድር ተሰግቷል። በኬንያ ለምርጫ ማካሄጃና ቅስቀሳ የሚወጣው ወጪ በዓለም ከፍተኛ ከሚባሉት አንዱ ነው።
ዛሬ እየተካሄደ ላለው ምርጫ የተደረገው የምረጡኝ ዘመቻ ያበቃው ፓርቲዎች ያላቸውን ከፍተኛ ሃብት “እዩልኝ” በማለት ባደረጉት ታይታ ነው። የኢኮኖሚ ችግርና በደሃውና በሃብታሙ መሃከል ያለ ልዩነት የሰፋ ቢሆንም፣ በኬንያ ለምርጫ የሚወጣው ወጪ በዓለም ካሉት ከፍተኛ የምርጫ ወጪዎች አንዱ ነው። ይህም በኬንያ ዲሞክራሲያዊ እድገት ላይ ተጽእኖ እንዳያሳድር ሥጋት ፈጥሯል።
ባለሞያዎች እንደሚሉት፣ በኬንያ የምርጫ ዘመቻ በአየርና በምድር ላይ የሚከናወነው የሃብት ታይታ፣ ተነጻጻሪ ያልተገኘለት ነው።