በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬንያ ምርጫ ውዝግብ አርግዟል


ኬንያውያን ትናንት ያካሄዱትን የምርጫ ውጤት እንዳይቀበሉ፣ ዋናው የተቃዋሚ መሪና ፕሬዚዳንት፣ ዕጩ ተወዳዳሪው ራይላ ኦዲንጋ ጥሪ አሰሙ፡፡

ኬንያውያን ትናንት ያካሄዱትን የምርጫ ውጤት እንዳይቀበሉ፣ ዋናው የተቃዋሚ መሪና ፕሬዚዳንት፣ ዕጩ ተወዳዳሪው ራይላ ኦዲንጋ ጥሪ አሰሙ፡፡

ከተሰጠው ድምፅ 96 ከመቶው የተቆጠረ ሲሆን፣ ሥልጣን ላይ ያሉት ፕሬዚዳንት አሁሩ ኬንያታ 54 ለ45 በሆነ ልዩነት እየመሩ መሆናቸው ተዘግቧል፡፡

የተቃዋሚ መሪና ፕሬዚዳንት፣ ዕጩ ተወዳዳሪው ራይላ ኦዲንጋ
የተቃዋሚ መሪና ፕሬዚዳንት፣ ዕጩ ተወዳዳሪው ራይላ ኦዲንጋ

በሌላ በኩል ደግሞ ከምርጫው ጋር የተያያዙ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ቢከሰቱ ፖሊስ አላስፈላጊ ያልሆነ ኃይል እንዳይጠቀም ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ቡድን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አሳስቧል፡፡

የኬንያ ብሄራዊ የምርጫ ኮሚሽን ውጤቱን ዛሬ እንደማያሳውቅ ማምሻውን ገልጿል። ቀደም ሲልም ውጤት ዛሬ የመግለፅ ዕቅድ እንዳልነበረው ኮሚሽኑ አመልክቶ በSMS ማለትም በቴክስት የተላለፈው ዜናም የሃሰት መሆኑን አመልክቷል።

ናሳ በሚል ምኅፃር የሚጠራው የ “ብሄራዊ የላቀ ጥምረት” ዕጩ የሆኑት ሚስተር ራይላ ኦዲንጋ የምርጫ ኮሚሽኑ የመጨረሻውን ውጤት ከተሰጡት ድምፆች ጋር የሚቀርቡለትን ቅፆችና ሠነዶች ሳያረጋግጥ አጠቃላዩን ውጤት እንዳያሳውቅ አሳስበዋል።

“ሕዝባችን ውጤቶቹን እንዳይቀበል እየነገርነው ነው፤ የፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የገዥዎችና የአካባቢ ምክር ቤቶች ምርጫዎች ውጤቶች ሁሉ ባዕድ ቁጥሮች ናቸው” ብለዋል።

ገዥው ጁቤሊ ፓርቲ “በሃገሪቱ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ማጭበርበር ፈፅሟል” ያሉት ኦዲንጋ ይሁን እንጂ ደጋፊዎቻቸው እንዲረጋጉና ተረጋግተው እንዲቆዩ አሳስበዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ የፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ፓርቲ የሆነው ጁቤሊ ዋና ፀሐፊ ራፋኤል ቱጁ በሰጡት መግለጫም እንዲሁ በሁሉም ወገን መረጋጋት እንዲኖር አሳስበዋል።

የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ
የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ

የምርጫ ኮሚሽኑ ሊቀመንበር ዋፉላ ቼቡካቲ በሰጡት መግለጫ የተቃዋሚው ጥምረት ናሳ እያናፈሰ ያለው ከምርጫ ሂደቱ አንዷን ጉዳይ፣ የውጤቶቹን መነገር አስመልክቶ እንጂ በአጠቃላዩ ምርጫ ሂደት ላይ አለመሆኑን አመልክተዋል።

ጊዜያዊ ውጤቶቹን ለመግለፅም እየተጠቀሙ ያሉት የምርጫውን ሰነዶች ዋና ቅጂዎች እየፈተሹ መሆኑን ተናግረዋል።

በአጠቃላይ በመላ ሃገሪቱ ያለው ሁኔታ የተረጋጋ መሆኑ ቢገለፅም በምዕራባዊቱ ኪሱሙ ከተማ ውስጥ ግን የተቃውሞ ሰልፎች እንደነበሩና ፖሊስ አስለቃሽ ጋዝ መርጨቱ ተዘግቧል።

በናይሮቢ ማታሬ መንደርም እንዲሁ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች እንደታዩ ታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎችን ለመበተን ፖሊስ ኃይል ወይም ጥይት ከመጠቀም እንዲቆጠብ፣ ኃይል መጠቀም የመጨረሻው አማራጭ መሆን እንዳለበትና ያም ቢሆን የሰውን ሕይወት ከጉዳት ለማዳን ሲያስፈልግ ብቻ እጅግ አነስተኛ ኃይል እንዲሆን የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅ አፍሪካ፣ የአፍሪካ ቀንድና የታላላቅ ሐይቆች አካባቢ ዳይሬክተር ሙቶኒ ዋንዬኪ አሳስበዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኬንያ ምርጫ ውዝግብ አርግዟል
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:00 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG