በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኬንያዊያን መሪዎቻቸውን እየመረጡ ነው

ኬንያዊያን ለሃገሪቱ ፕሬዚዳንትነት የሚደረገውን ፉክክር ጨምሮ ለስድስት የሥልጣን ቦታዎች በ46ሺ 232 የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ላይ ዛሬ ድምፅ እየሰጡ ነው።

ለምርጫው 22.1 ሚሊዮን ድምፅ ሰጭ መመዝገቡን የምርጫ ኮሚሽኑ አስታውቋል።

ምርጫው በአጠቃላይ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑ ቢነገርም አንዳንድ ችግሮች መኖራቸውን የሚጠቁሙ ሪፖርቶችም እየተሰሙ ነው።

ማለዳ ላይ የምርጫ ጣቢያዎች እንደተከፈቱ ብዙም ሳይቆይ ናኩሩ አውራጃ ሮይንጋይ ምርጫ ወረዳ ውስጥ ለህዝብ እንደራሴነት በሚደረገው ውድድር የድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ ስህተት በመገኘቱ ምርጫው እንዲቋረጥ ተደርጓል።

የወረዳው የፓርላማ መቀመጫ ድምፅ አሰጣጥ መስተጓጎል ያበሳጫቸው ነዋሪዎች መንገዶችን በመዝጋትና አጥንቶችን በእሳት በማያያዝ የምርጫ ኮሚሽኑ ባስተላለፈው ትዕዛዝ ላይ ተቃውሟቸውን ገልፀዋል።

ሌሎችም አራት የፓርላማ መቀመጫ ድምፅ አሰጣጥ ሂደቶችም እንዲሁ በድምፅ ወረቆቶች ላይ በተገኙ ስህተቶች ምክንያት እንዲቋረጡ መደረጉ ታውቋል።

በሌላ በኩል ማዕከላዊ ኬንያ ውስጥ ያለው የመራጮችን ማንነት መለያ መሣሪያ ለምክትል ፕሬዚዳንትነት ከዊሊያም ሩቶ ጋር ተጣምረው እየተወዳደሩ ያሉትን ሪጋቲ ጋቻጓን የጣት አሻራ መለየት አለመቻሉ የተገለፀ ሲሆን ወረቀት ላይ በሰፈረው የመራጮች መዝገብ ውስጥ ማንነታቸው በመረጋገጡ ድምፃቸውን መስጠት መቻላቸው ታውቋል።


ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG