በኬንያ በጎርፍ ምክያት የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ200 በላይ እንዳሻቀበ የአሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒሲቴር ሲያስታውቅ፣ ወደ ጎረቤት ታንዛኒያ በመጠጋት ላይ ያለው አውሎ ነፋስም ስጋት ፈጥሯል።
በምሥራቅ አፍሪካ በመጣል ላይ ያለው ከፍተኛ ዝናብ ጎርፍ በማስከተሉ፣ ሰብልና መኖሪያ ቤቶች ሲወድሙ፣ በሺሕ የሚቆጠሩ ተፈናቅለዋል።
ባለፈው ሳምንት መጨረሻም በአዲስ አበባ አራት ሰዎች በጎርፍ አደጋ መሞታቸው ይታወሳል።
በኬንያ ባለፉት 24 ሰዓታት 22 ሰዎች ሲሞቱ፣ ከዝናብና ጎርፍ ጋራ በተያያዘ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 210 መድረሱን የአሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚንሲቴር ዛሬ ዓርብ አስታውቋል።
165 ሺሕ ሰዎች ሲፈናቀሉ፣ 90 የሚሆኑት የደረሱበት አልታወቀም ተብሏል።
በዱባይ ደግሞ በአንድ ወር ውስጥ ለሁለተኛ ግዜ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክያት በርካታ በረራዎች መሰረዛቸውን አንድ የአየር ማረፊያው ባለሥልጣን አስታውቀዋል።
ሠራተኞች ከቤት ሆነው እንዲሠሩ፣ ትምህርት ቤቶችም በኢንተርኔት ማስተማራቸውን እንዲቀጥሉ የዱባይ ባለሥልጣናት የትላንቱ ዝናብ ከመጣሉ አስቀድሞ ማሳሰቢያ አውጥተዋል።
መድረክ / ፎረም