ሀዋሳ —
በደቡብ ክልል ከፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ከ20 ሺህ በላይ የከምባታና ጠምባሮ አርሶአደሮች በማንነታችን ጥቃት ደርሶብናል በማለት እየተፈናቀሉ ናቸው፡፡
አርሶአደሮቹ የተፈናቀሉት ከሶስት ሳምንት በፊት በወረዳው ከ30 በላይ ሲቪሎች በታጠቁ ግለሰቦች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡
ጉዳያችንን ለክልሉ መንግሥት ብናሳውቅም ችላ ተብለናል ሲሉ አርሶአደቹ ተናግረዋል። አሁን ለችግር መጋለጣቸውንም ለቪኦኤ አስረድተዋል፡፡
የከምባታ ጠንባሮ ዞን በበኩሉ የተፈናቀሉ ዜጎች በስቃይ ላይ መሆናቸውን ገልጦ መፍትሔ እየተፈለገ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ