በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዝሆን ጥርስና የአውራሪስ ቀንድ ሕግ ወጥ ንግድ መርማሪ ኬንያ ውስጥ ተገደሉ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ከዓለም እጅግ የታወቁ የዝሆን ጥርስና የአውራሪስ ቀንድ ሕግ ወጥ ንግድ መርማሪዎች አንዱ፣ ኬንያ ውስጥ ተገደሉ።

ከዓለም እጅግ የታወቁ የዝሆን ጥርስና የአውራሪስ ቀንድ ሕግ ወጥ ንግድ መርማሪዎች አንዱ፣ ኬንያ ውስጥ ተገደሉ። ኤዝመንድ ብራድሊ ማርቲን ናይሮቢ የመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ አንገታቸው ላይ በስለት ተወግተው ተገድለው ነው የተገኙት ።

የሰባ አምስት ዓመቱ አሜሪካዊ ሕገወጥ የዝሆን ጥርስ ንግድ እና ገበያዎቹ ላይ፣ በድብቅ ያደረጉት ክትትል ድርጊቱን ለማጋለጥ አስችሏል።

ዋይልድላይፍ ዳይሬክት የተባለው ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ፓውላ ካሁምቡ የማርቲን ሥራ በቅርቡ ዩናይትድ ስቴትስ ኮንጎ ቪየትናም ናይጄሪያ አንጎላ እና ቻይና ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የዝሆን ጥርስ ነጋዴዎችን ለማጋለጥ እንደረዳ ገልፀዋል።

ቻይና እኤአ በ1993 ሕጋዊ የአውራሪስ ቀንድ ንግድ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ሕጋዊ የዝሆን ጥርስ ንግድ ለመከልከል ያበቃት የሳቸው ሥራ ውጤት እንደሆነ ተነሯል።

የዝሆን ጥርስና የአውራሪስ ቀንድ ሕግ ወጥ ንግድ መርማሪ ኬንያ ውስጥ ተገደሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:12 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG