የኢጣልያ መንግሥትና ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያኗ በጋራ በመሆን፣ አፍሪካውያን ስደተኞች ወደ ሀገሪቱ የሚገቡበትን መንገድ የሚያመቻች አዲስ ዘዴ ለመፍጠር እየተሰባሰቡ ናቸው።
በዚህ “ሰብዓዊ መተላለፊያ” ባሉት ዕቅድ መሠረት ኢትዮጵያ መጠለያ ካምፕ ውስጥ የሚኖሩ ከኤርትራ፣ ከሶማልያና ከደቡብ ሱዳን የሆኑ ወደ 500 ስደተኞች ወደ ኢጣልያ የሚዘዋወሩቡበትን መንገድ እያመቻቹ ናቸው።
ሮም የምትገኘው ዘጋቢ ጆሴፒኒ ማክኬናለአፍሪካ ክፍል ባልደረባ ኪም ሌዊስ እንደገለፀችው፤ ሂደቱ እስከ ሁለት ዓመት እንደሚራዘምም ታውቋል።
ኪም ከዦሴፊን ጋር ያካሄደችውን አጠር ያለ ቃለ ምልልስ አዲሱ አበበ ያቀርበዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ