በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢንተርኔት መቋረጥ በኢትዮጵያ


በኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ ከተሞች በተለይ ደግሞ በአሮሚያና በአማራ የተለያዩ ከተሞች የስልክ ኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ከተቋረጠ ወራት መቆጠሩን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።

የኢትዮጵያ መንግሥት በተደጋጋሚ የኢንተርኔት አገልግሎትን በመዝጋትና ማኅበራዊ ሚዲያን በማገድ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ መስተጋብሮችን ያስተጓጉላል፣ አፈናን ያብብሳል፣ መረጃ በተገቢው መንገድ ወደ ሕዝብ እንዳይደርስም ይቆጣጠራል ሲሉ ባለሞያዎች ይተቹታል።

በኢንተርኔት አገልግሎት ላይ ጥናት የሚሰሩ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፤ ኢትዮጵያ የኢንተርኔት ነፃነት የሌለባት፣"ኢንተርኔትን" በውድ ዋጋ የምትሸጥ ሀገር ይሏታል።

የኢትዮጵያ ኢንተርኔት አገልግሎት አነስተኛ መሆኑን በተጨማሪም ውድ በመሆኑ አገልግሎቱን በሚፈለገው መጠን ዜጎች ሊጠቀሙበት እንደማይችሉ ከዚህ የተረፈው ላይ ገደብ ሲጣልበት ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ የኢንተርኔት አገልግሎት አለ ማለት እንደማይቻል ይናገራሉ።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ)

የኢንተርኔት መቋረጥ በኢትዮጵያ
please wait

No media source currently available

0:00 0:13:13 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG