በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በግዴታ የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 65.3 ሚሊዮን መድረሱ ተገለጸ


ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ስዎች ብዛት
ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ስዎች ብዛት

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ ኮሚሽን በዛሬው ዕለት ተከብሮ የዋለውን የዓለም የስደተኞች ቀን ምክንያት በማድረግ ባወጣው አዲስ ሪፖርት፤ ባለፈው ዓመት ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ስዎች ብዛት ከምንጊዜውም የላቀ መኾኑን ገለፀ። ግጭትና የፖለቲካ አለመረጋጋት ለመፈናቀላቸው ዋና ምክንያት እንደሆን ሪፖርቱ ይዘረዝራል።

ባለፍው የአውሮፓውያኑ 2015 ዓ.ም ብቻ ከቤት ንብረታቸው በግዴታ የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 65.3 ሚሊዮን እንደሚደርስ በሪፖርቱ የገለጸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን በዚህ ዓመት ደግሞ ይህ ቁጥር በ5 ሚሊዮን መጨመሩን ያስረዳል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን ከፍተኛ ኮሚሽነርና የስደተኞች ጉዳይ ኃላፊ ፊሊፖ ግራንዲ ከ113 ሰው አንዱ ወይ አገር ውስጥ እያለ ተፈናቅሏል አሊያም ስደተኛ እንደሆን ይናገራሉ። በተለያዩ ሀገሮች ባለው የፖለቲካ አለመረጋጋትና ግጭት ሰዎች ከቀያቸው ለመፈናቀል እየተገደዱ እንደሆነ የሚናገሩት ኃላፊው ይህ እየሆነ ያለው ደግሞ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሀገሮች ድንበራቸውን አጥብቀው እየዘጉና ስደተኞችን ወደ ሀገራቸው ላለማስገባት በሚከላከሉበት ጊዜ ነው ብለዋል።

የስደተኞች ቁጥር- ሪፖርት
የስደተኞች ቁጥር- ሪፖርት

“በእያንዳንዷ ደቂቃ 24 ሰዎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው ከቀያቸው ይፈናቀላሉ። ከነዚህ ውስጥ ሁለት ሶስተኛውን ቁጥር የሚይዙት ደግሞ ሀገር ውስት የሚፈናቀሉት ናቸው። 90 በመቶ የሚሆኑት ከደሃና መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት የሚፈናቀሉ ናቸው። በሀብታም ሀገራት ይህ ሁኔታ አያጋጥምም ።”

ሪፖርቱ እንደሚያስረዳው ከጠቅላላው የዓለም ስደተኞች ቁጥር ወደ 10 ሚሊዮን የሚሆኑት ሦርያውያን ሲሆኑ፣ ከዚህ ውስጥ 3 ሚሊዮን ወደ ጎረቤት ሀገሮች የተሰደሱ ቀሪዎቹ ደግሞ እዚያው ሀገር ውስጥ የተፈናቀሉ መሆናቸው ታውቋል።

ሦርያውያኝ ከሚጨምረው 21 ሚሊዮን የስደተኞች ቁጥር ግማሹ ከአፍጋኒስታንና ሶማልያ የሚሰደዱ መሆናቸውን ተካቷል። በተጨማሪም ከእነዚህ ስደተኞች ውስጥ 50 በመቶ የሚሆኑት ሕጻናት መሆናቸውንና አብዛኛዎቹ ደግሞ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የተለያዩ መሆናቸውን ይጠቅሳል።

ኮሚሽነር ግራንዲ ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት ቃል መሰረት ሶርያ በቀያቸው የሚፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር የመጀመርያው ደረጃ ያይዘች ስትሆን ቁጥሩ አሁንም እየጨመረ መሆኑን ገልጸዋል።

ሪፖርቱ አክሎም ባለፈው ዓመት ጥገኝነት ከጠየቁት ስደተኞች 98,000 ጠባቂ የሌላቸው ህጻናት መሆናቸውን ይህ ቁጥር አሁንን ይጨመረ መሆኑን ያስረዳል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ተቋም ከፍተኛ ኮሚሽን ፊሊፖ ግራንዲ የሰጡት መግለጫ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:16 0:00

በስደተኞች ተቋሙ ሪፖርት መሰረት ከመካከለኛው ምሥራቅና ከሰሜን አፍሪቃ የሚሰደዱና ከቀያቸው የሚፈናቀሉ ሰዎች ቁትር 23.6 ሚሊዮን መሆኑን በመላው ዓለም ከፍተኛ የተፈናቃዮች ቁጥር መሆኑን ታውቋል።

የከሰሃራ በታች ያሉ አገሮች በ18.4 የስደተኞችና የአገር ውስትጥ ተፈናቃዮች ቁጥር ሁለተኛ ደረጃን የሚይዙ መሆኑ የገለጸው ሪፖርት ምንም እንኳን አውሮጳ በስደተኞች ቁጥር አብዛኛውን የመገናኛ ብዙሃን ሽፋን ታግኝ እንጂ አሕጉሪቷ አነስተኛ የስደተኞች ቁጥር ካላት ሀገሮች አንዷ መሆኗን ያስረዳል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

በግዴታ የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 65.3 ሚሊዮን መድረሱ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:46 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG