በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"መስፈርቶችን አሟልቶ ፈቃድ የተከለከለ ድሮን የለም" - ኢንሳ


የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው
የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው

የመቀሌ ዩኒቨርስቲ ያስመጣው አንድ ሰው አልባ በራሪ ቁስ ወይም ድሮን ፈቃድ ያላገኘው የደኅንነት መስፈርቶችን ባለማሟላቱ እንደሆነ የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ /ኢንሳ/ ዋና ዳይሬክተር አስታውቋል።

ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ለአሜሪካ ድምፅ እንዳስታወቁት ዩኒቨርስቲው ያስመጣው ድሮን መጠን ግለስቦችና ተቋማት ሊይዙት ከሚፈቀደው በላይ ነው።

ጉዳዩ የፌደራል ተቋም ከሆነው መቀሌ ዩኒቨርሲቲ እንጅ ከትግራይ ክልል ጋር የተገናኘ እንዳልሆነ ያስታወሱት ዋና ዳይሬክተሩ ምላሹም በጊዜው መገለፁን አመልክተዋል።

ይሄም ሆኖ ፌደራል መንግሥቱ ትግራይን ጨምሮ የአንበጣ መንጋ በተከሰተባቸው የሃገሪቱ አካባቢዎች በድሮን እና በአውሮፕላን የታገዘ የኬሚካል ርጭት እያካሄደ መሆኑን ዶ/ር ሹመቴ ተናግረዋል።

የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ/ኢንሳ/ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛውን በስልክ አነጋግረናል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

"መስፈርቶችን አሟልቶ ፈቃድ የተከለከለ ድሮን የለም" - ኢንሳ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:59 0:00


XS
SM
MD
LG