ዋሽንግተን ዲሲ —
አሚና ሙስታፍ እና ቤተሰቦችዋ ጎርፍ ካፈናቀላቸው ሦስት ዓመት አለፋቸው፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ መኖሪያቸው የሞቋዲሾው መጠለያ ጣቢያ ሆኗል፡፡ ሶስት ሳምንት የሞላው ልጇ ክትባት ያስፈልገዋል፡፡ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሳቢያ ግን ወደ ህክምና መስጫ ጣቢያዎቹ መሄድ አልደፈረችም፡፡ ይሄ ፍርሃት እሷ ባለችበት የመጠለያ ጣቢያ ውስጥ ባሉት ሰዎች ሁሉ ያደረ መሆኑን ትናገራለች፡፡ እንዲህ ትላለች አሚና
እኔ ወደ ጤና እንክባቤ መስጫ ተቋማቱ መሄድ አልቻልኩም፡፡ ምክንያቱም ኮቪድ-19 መላውን ዓለም እየወረረ ነው፡፡ ለራሴም ሆነ ለልጄ ጤንነት እፈራለሁ፡፡ ወደ ጤና ተቋማቱ በመሄድ ቫይረሱ እንዲይዘን አንፈልግም፡፡ በዚሁ በኮቪድ-19 የተነሳ እኔም ሆንኩ ልጄ የቅድመ ወሊድም ሆነ ከወሊድ በኋላ ያለው አስፈላጊ የጤና እንክብካቤ አምልጦናል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።