የዓለም ስጋት በሆነው የኮሮና ቫይረስ ምክንያት በአስደንጋጭ ሁኔታ ቀንሶ የነበረው የደም ለጋሾች ቁጥር ባለፉት ሦስት ሳምንታት ውስጥ ከፍተኛ መሻሻል አሳይቷል።
የብሄራዊ ደም ባንክ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ያረጋል በንቲ ለቪኦኤ እንደገለፁት፣በለጋሾች ቁጥር መመናመን ምክንያት ትልቅ አደጋ ውስጥ ወድቆ የነበረው የደም ባንክ ተከታታይ ባደረገው ኅብረተሰቡን የመቀስቀስ ሥራ ወደ ባንኩ እየሄደ ደም የሚሰጠው ሰው ጨምሮ የደም ክምችት15 ሺህመድረሱንያስረዳሉ።
የኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ ከመግባቱ በፊት አዲስአበባ ውስጥ በየዕለቱከ300 እስከ350ደም እንዲለገስ ይፈለግ ነበር። በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ግን ሆስፒታሎች በቀጠሮ የሚደረጉ ቀዶ ጥገናዎችን በመቀነሳቸው የደምፍላጎቱ ወደ 150 ወርዶ ነበር።"የደም ባንኩ ግን ይሄንንም ለማሟላት ትግል ላይ ነበር ”ያሉት አቶ ያረጋል“አሁንግንባንኩበ50 ዓመቱ አይቶት የማያውቀው ሰው ቁጥር በቀን ውስጥ በፈቃደኝነት እየሰጠነው” ይላሉ።
“ደም በባህሪው ከሳምንታት በላይ መቆየት አይችልም”ያሉት አቶ ያረጋል፣ባንኩ የደም ክምችቱ ከሚፈለገው በላይ ከሆኑባቸው ከተማዎች ወደ ሌሎች ከተማዎች እያዘዋወረ በመላው ሀገሪቱ በቂ የደም አቅርቦት እንዲኖር እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
‘በኮሮና ከሚሞተው በበለጠ በደም ማጣት የሚሞቱ እናቶች ቁጥር እንዳይጨምር ጥንቃቄ ይደረግ’ በማለት ጥሪ አቅርቦ የነበረውና80 በመቶ የደም ለጋሾቹ በመቀነሳቸው ደም የሚያቀርብላቸው25 ሆስፒታሎች ሙሉ ለሙሉ የቀዶ ጥገና አገልግሎት እንዲያቋርጡ አርጎ የነበረው፣የባህርዳር ደም ባንክነው። የደም ባንኩ ኃላፊ አቶ ምትኩ ሽፈራው እንደነገሩን በቀን እስከ400 የደም የለጋሾች የነበረው ባንኩ፣በኮሮና ቫይረስ ምክያት ቁጥሩ ወርዶ አምስት በመድረሱ ሕዝባዊ ጥሪ ተላልፎ፣ባለፉት ሁለት ሳምንታት እስከ669 ደም መሰብሰብ ተችሏል።
አቶ ምትኩ አሁን ያለው በቂ ክምችት አስተማማኝነቱ ለሁለት ሳምንት ነው፣ደም አንዴ ተሰብስቦ ለረጅም ጊዜ የሚቀመጥ ባለመሆኑ የደም ባንኩ በየሳምንቱ በቂ ለጋሾችን ይፈልጋል ይላሉ።
በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ በሚገኝበት የሱማሌ ክልል የሚገኘው የጅጅጋ ቅርንጫፍ ደምባንክም የኮሮናቫይረስ ከመግባቱ በፊትም ያገኝከ ነበረው የደም ለጋሾች ቁጥር በላይ እያገኘ መሆኑን የነገሩን ደግሞ በሱማሌ ክልል ጤና ቢሮ የደም ባንክ ሥራ ሂደት ኃላፊ አቶ ዚያድኑር አብዲናቸው።
የኮሮናቫይረስ በፈጠረው መደናገጥ ህብረተሰቡ ደምከመስጠት በታቀበበት ወቅት ግምባር ቀደም ሆነው በፈቃደኝነት ደም ከለገሱ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች አንዱ የሆነው ዮናስ ታደሰ ነው።ዮናስ "ደም በችግር ጊዜ ብቻ ሳይሆን በቋሚነት መለገስ አለበት"ይላል።
ደም ሲያጥር በጤና ተቋማትና በበሽተኞች ላይ የሚፈጠረው ጫናእ ጅግ ከፍተኛ ይሆናል የሚሉት የደም ባንክ ኃላፊዎቹ ለሚቀጥሉት ሁለትና ሦስት ሳምንታት በቂ የደም ክምችት መፍጠር ቢቻልም፣የደም አገልግሎት ዘመን በጣም ውሱን በመሆኑ ሰዎች በየጊዜውና በየእለቱ ደም መለገሳቸውን እንዳያቋርጡ ጥሪ አስተላልፈዋል።
(ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ይጫኑ)