የምሥራቅ አፍሪካ ሃገሮች የጋራ ልማት ትብብር /ኢጋድ/ ባለፈው ቅዳሜ ባካሄደው ስብሰባ ወደ ሀገራቸው በፍላጎታቸው ለሚመለሱ የሶማልያ ተወላጆች ሁኔታዎችን ለማመቻቸትና ሶማልያ ውስጥ ስላለው የፖለቲካና የፀጥታ ሁኔታ መፍታኄ ለማበጀት ተስማምተዋል።
ስምንት የምሥራቅ አፍሪካ ሀገሮች በክልሉ ሰላሉት ሶማልያውያን ስደተኞች ሁኔታ ለመነጋገር ነበር የተሰበሰቡት፡፡ ስብሰባው የተደረገው የኬንያ መንግሥት ዳዳብ የስደተኞች መንደርን ከመዝጋቱ ከሁለት ወራት በፊት ነው፡፡
ሪፖርተራችን ሞሐመድ ዮሱፍ ከናይሮቢ የላከውን ዘገባ አዳነች ፍሰሀየ ታቀርበዋለች።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ