ዋሺንግተን ዲሲ —
በኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ አካባቢያዊ ጣልቃ ገብነት ወይንም እገዛ የሚፈገልግ አይደለም ይላሉ የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ማሁቡብ ማአሊም - የኢትዮጵያ ሁኔታ የሀገሪቱ መሪዎች ራሳቸው መፍትኄ እያፈለጉለት ያለ ጉዳይ ነው ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡
ከጠ/ሚኒስትሩ ሥልጣን መልቀቅ እና የመፍትሄው አካል ለመሆን እፈልጋለሁ ከማለታቸው በላይ ምን ዓይነት ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ይፈለጋል ሲሉም ጠይቀዋል፡፡ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግሥታት ባለሥልጣን ኢጋድ ለግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያ በመከላከል ሥራ ላይ ላተኮረ ዲፕሎማሲና ለአደራዳሪነት ፕሮግራሞቹ የሚሆን የ42 ሚሊዮን ዩሮ ሥምምነት ከአውሮፓ ኅብረትና ከኦስትሪያ ልማት ድርጅት ጋር ተፈራርሟል፡፡
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ