በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተፈናቃይ ቁጥር ጨምሯል


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

በኢትዮጵያ የውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር ከግማሽ ሚሊየን መብለጡት አይ.ዲ.ኤም.ሲ. በሚል ምኅፃር የሚጠራው ተቀማጭነቱ ጄኔቫ ስዊትዘርላንድ የሆነ የውስጥ ተፈናቃዮች ክትትል ማዕከል አስታውቋል።

በኢትዮጵያ የውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር ከግማሽ ሚሊየን መብለጡት አይ.ዲ.ኤም.ሲ. በሚል ምኅፃር የሚጠራው ተቀማጭነቱ ጄኔቫ ስዊትዘርላንድ የሆነ የውስጥ ተፈናቃዮች ክትትል ማዕከል አስታውቋል።

የመፈናቀሎቹ አበይት ምክንያቶች የመረጋጋት መጥፋትና ድርቅ መሆናቸውን የጠቆመው ይህ ማዕከል በዓለም ዙሪያ በአውሮፓ አቆጣጠር በ2017 ዓ.ም. ከዘጠኝ ሚሊየን ሰው በላይ ከየአካባቢው መፈናቀሉን አስታውቋል።

የዛሬ ሃያ ዓመት የተቋቋመውና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እውቅና የተሰጠው የውስጥ ተፈናቃዮች ቃፊሩ ማዕከል አይዲኤምሲ ረቡዕ፣ ነኀሴ 10/2009 ዓ.ም. ባወጣው የግማሽ ዓመት ማሳያ ሪፖርት ባለፉት ስድስት ወራት የተፈናቀሉው ሰው ቁጥር ባለፈው የአውሮፓ 2016 ዓ.ም. ሙሉ ዓመት የተመዘገበውን ሁለት ሦስተኛ እንደሚያክል ጠቁሟል።

ይህ አራት ሚሊየን ተኩል የሚሆን ቁጥር ያለው ሰው የተፈናቀለው በአመዛኙ በግጭቶች ምክንያት መሆኑን የማዕከሉ የፖሊሲና የምርምር ኃላፊ ቢና ዴሳዪ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

የዘንድሮው የመፈናቀል መጠን አይሎ የተገኘባቸውን አሥራ አንድ ሃገሮች አይዲኤምሲ ባወጣው የፕሬስ መግለጫ ነጥሎ የጠራ ሲሆን ኢትዮጵያን በዓለም ዙሪያ ካለው የውስጥ መፈናቀል በአምስተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል።

“በ2017 ዓ.ም. [በአውሮፓ የዘመን አቆጣጠር] የመጀመሪያ ግማሽ ባየነውና በመዘገብነው መሠረት ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ሁለት መቶ አሥራ ሦስት ሺህ ሰው ነው የተፈናቀለው። ይህ ደግሞ ባለፈው 2016 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ከነበረው የሙሉው ዓመት ቁጠር ጋር እኩል ነው” ብለዋል ዴሳዪ።

ኃላፊዋ ምክንያቶቹን ሲናገሩ በሃገሪቱ ውስጥ በዓመቱ የታየው አለመረጋጋት፣ ፀረ-መንግሥት አመፅና የታጠቀ እንቅስቃሴ የዛሬ ሃያ ዓመት ይታይ ከነበረው በሦስት እጥፍ ያደገ እንደሆነ የገለፀውን የማዕከላቸውን ሪፖርት አጠናክረዋል።

“ሰዉን ለአደጋ፣ ለመጋለጥና ለመሰደድ የሚዳርገትና ሁኔታውንም የሚያባብሱት የምጣኔ ኃብትም ማኅበራዊና የአካልም ደኅንነት ማጣት ተዳምረው ለመሆኑ የኢትዮጵያ ገፅታ ጥሩ ማሳያ ነው” ብለዋል ቢና ዴሳዪ አክለው።

ኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክን፣ ኢራቅን፣ ሦሪያንና ፊሊፒንስን ተከትላ በሃገር ውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር አምስተኛ በሆነችው በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት በአጠቃላይ 588 ሺህ ተፈናቃዮች እንደሚገኙባት አመልክተዋል።

ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በተመዘገበው የውስጥ መፈናቀል ኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ውስጥ ብቻ ወደ አንድ ሚሊየን የሚጠጋ ሰው መፈናቀሉና በኢራቅ 922 ሺህ፣ በሦሪያ 629 ሺህ፣ በፊሊፒንስ 466 ሺህ ሰው መፈናቀሉን አይዲኤምሲ አመልክቷል።

በሁከት የሚታመሱት ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ጋምቢያ፣ አፍጋኒስታን፣ ናይጀሪያ፣ የመን፣ ሶማሊያ ደግሞ ኢትዮጵያን ተከትለው ከስድስተኛ እስከ 11ኛ ደረጃ ላይ ሠፍረዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የተፈናቃይ ቁጥር ጨምሯል
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:57 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG